top of page

The truth about Fano (militia) and the false accusations against it

Lij Tedla Melaku Worede

Articles in biased international newspapers have accused the Amhara Fano militia of committing massacres of ethnic others. Fano’s description on Wikipedia has also become a subject of controversy where arbitrary and dishonest descriptions of Fano painting it as a genocidal group have aroused controversy and fury as the Wikipedia page was locked to prevent any corrections or editing. The Wikipedia article, rather than fairly and justly explaining the history, ideology, and contexts of Fano’s struggle, focuses on criminalizing the group in what seems to build a case to globally defame and neutralize it, associating it with massacres that were committed by opposing forces.

Fano Zemene Kassie speeches' to members of Amhara Popular Forces

ከአማራ ፋኖ አንድነት በሸዋ እና ከአንድ አማራ ፋኖ የተሰጠ የጋራ መግለጫ

Who's Fano Eskinder Nega

Fano Eskinder Nega.JPG

እስክንድር ነጋ ማን ነው ?

እስክንድር ነጋ ፈንታ በ1960 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ተወለደ። አባቱ የአሜሪካው ሩትጋርት ባልደረባ ሲሆኑ እናቱ ደግሞ የአሜሪካ ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ቤሩት አስተማሪ ነበሩ። በኋላም በአዲስ አበባ የግል የጤና ተቋም አቋቁመው በመንግሥት ንብረቶቻቸው እስከወረሰባቸውና ሥራቸውን እስካስቆመበት ጊዜ ድረስ ሀገራቸውን በብዙ አገልግለዋል። እስክንድር እድሜው ለትምህርት ሲደርስ አዲስ አበባ በሚገኘው ሳንፎርድ ኢንግሊሽ ስኩል መማር ጀመረ። ትምህርት ቤቱ የተሻለ የትምህርት ጥራት እና የትምህርት መርጃ መሣሪያዎች አሉት፡፡ በሙያዊ ብቃታቸው የተመሰገኑ መምህራን ያሉት ሲሆን ተማሪዎችን ለማስተማር ት/ቤቱ የሚያስከፍለው ገንዘብም ከሌሎች ት/ቤቶች ሲነፃፀር ከፍተኛ የሚባል ነው። የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን በዚሁ አጠናቆ የ2ኛ ደረጃ ትምህርቱን በሰሜን አሜሪካ ተምሯል። ከዚያም ዋሽንግተን በሚገኘው አሜሪካን ዩኒቨርሲቲ በመግባት 'ኢኮኖሚክስ' እና ፖለቲካል ሳይንስ አጥንቶ የማስተርስ ዲግሪውን ይዟል። በተማሪነት ጊዜውም የደርግን አምባገነናዊ ሥርዓት በመታገል አሳልፏል። የወታደራዊው አስተዳደር ደርግ መንግሥት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን በከስክስ ጫማው ሲቀጠቅጥ ‹‹ለምን?›› በማለት ተቃውሟል። ቤተሰቦቹም ቢሆኑ ይህንኑ ሥርዓት አምርረው ተቃውመዋል። በአሜሪካ አደባባዮች በተደረጉ ደርግን የሚቃወሙ ሰላማዊ ሰልፎች እስክንድር ከነቤተሰቦቹ የፊት ተሰላፊ ነበር። የሀገሩ ጉዳይ የሚያሳስበው እስክንድር ነጋ በ1983 ዓ.ም. የመንግሥት ለውጥ መደረጉን ተከትሎ ከአሜሪካ ወደ አዲስ አበባ ተመለሰ። ከጋዜጠኛ ተፈራ አስማረ ጋ በመሆን በ1985 ዓ.ም. 'ኢትዮጲስ' የተባለች ሳምንታዊ የፖለቲካ ጋዜጣ አቋቁመው የወያኔን ሀገር አፍራሽ አገዛዝ መቃወም ጀመሩ። ጋዜጣዋ በሕዝብ እጅግ ተወዳጅ ነበረች። የተጻፈላት መሸጫ ዋጋ 75 ሳንቲም ቢሆንም በሽሚያ እስከ 7 ብር ድረስ ትሸጥ ነበር። ሆኖም የመንግሥት አፈና የገጠማት ገና በሁለተኛዋ ዕትም ነበር። የታፈነችው ጋዜጣዋ ብቻ አይደለችም፤ እስክንድርም በተደጋጋሚ ይታሰርና ይፈታ ጀመር። አንደኛውን ጋዜጣ ሲዘጉት ሌላ እያቋቋመ በፅናት ለፕሬስ ነፃነት ታገለ። ሐበሻ ፣ ምኒልክ ፣ አስኳል ፣ ሳተናው እና ወንጭፍ የተባሉ ጋዜጦችን ማዘጋጀቱን ቀጠለ። እስክንድር በሥራ አስኪያጅነት በሚመራው ሰርካለም አሳታሚ ሥር ከሚታተሙ ጋዜጦቹ መካከል ምኒልክ ፣ አስኳልና ሳተናው በተመሳሳይ ጊዜ ይታተሙ ነበር። ከሀበሻ በስተቀር ሌሎቹ ጋዜጦች በአማርኛ የሚታተሙ ሲሆን ሐበሻ ጋዜጣ በእንግሊዝኛ ነበር የምትታተመው። በይዘት ከሌሎቹ ጋር ተመሳሳይ ነች ፤ ልዩነቱ የቋንቋ ነው። ብዙ ጊዜ በእንግሊዝኛ የሚታተሙ ጋዜጦች በምሥራቅ አፍሪቃ ፖለቲካ እና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ የማተኮር ዝንባሌ አላቸው። ሐበሻ ግን ሙሉ ትኩረቷ ኢትዮጵያ ላይ ብቻ ነበር። ሀበሻ ጋዜጣ ተነባቢነቷ ሲጨምር በአማርኛም ለማሳተም እንቅስቃሴዎች ተጀመሩ። በአማርኛ ልትጀምር መሆኗን የሚያበስር ማስታወቂያ ‹‹ጎበዝ አምስት አመት ሞላን እኮ›› ከሚል ጉልህ ጽሑፍ ጋር በአዲስ አበባ ጎዳናዎች በየመብራት እንጨቶች ፣ በየአጥሩ እና በየግድግዳው ላይ ተለጠፈ። ማስታወቂያውን እስክንድር ከሌሎች ሰዎች ጋር ራሱ እየዞረ ነበር የለጠፈው። የሐበሻ ጋዜጣ ማስታወቂ በከፋፋይ ወያኔዎች ላይ ድንጋጤን ፈጠረ። በተለይ ‹‹ጎበዝ አምስት ዓመት ሞላን እኮ›› የሚለው አስከፋቸው። የሚችሉትን አደረጉና እስክንድርን አሠሩ። ጋዜጣዋም ሳትታተም በማስታወቂያ ቀረች።

Ethiopia’s Eskinder Nega named IPI Press Freedom Hero

Apr 25, 2017

Fano Eskinder Nega 2.JPG

Ethiopian journalist and blogger Eskinder Nega, who has been imprisoned since 2011 after criticising his country’s abuse of anti-terror laws to silence the press, has been named the International Press Institute (IPI)’s 69th World Press Freedom Hero.

Ethiopia: Freedom for journalist Eskinder Nega must lead to freedom for all prisoners of conscience

February 8, 2018

Fano Eskinder Nega 3.JPG

Commenting on breaking news from Ethiopia that journalist and Amnesty International prisoner of conscience Eskinder Nega will be among 746 prisoners released as part of a government pardon, Sarah Jackson, Amnesty International’s Deputy Regional Director for East Africa, the Horn and the Great Lakes, said: “It is wonderful news that this brave journalist will soon walk to freedom after seven years spent in jail simply for doing his job. He should not have spent a single day behind bars.

Eskinder Nega

Ethiopia

Fano Eskinder Nega 4.JPG

Eskinder Nega, a journalist and blogger based in Addis Ababa, was sentenced on July 13, 2012, to 18 years in prison for violating anti-terrorism laws after he criticized the government for arresting journalists and anti-government activists. He was jailed for almost seven years at Kaliti Prison in Addis Ababa, where political prisoners are housed with criminals and family visits are extremely limited, before being released on February 14, 2018, as part of a larger amnesty of political prisoners. On the evening of March 25, 2018, the Ethiopian Security Forces have re-arrested Eskinder and other journalists and politicians at a social event outside the capital, Addis Ababa. Eskinder was accused of displaying a prohibited national flag and gathering in violation of an official state of emergency but was later released without a charge on the evening of April 5th after spending 12 days of unwarranted, inhumane imprisonment.

Arrest and inhumane detention of Eskinder Nega an outrageous attack on Free Expression in Ethiopia 

March 29, 2018

Eskinder_Nega_(21892305546).png

NEW YORK—The re-arrest and inhumane detention of 2012 Freedom to Write Award honoree Eskinder Nega is an outrageous attack on the right of free expression in Ethiopia, and contravenes all recent positive progress the government has made toward creating a safe environment for independent voices, said PEN America in a statement today.

Who is Major Dawit Woldegiorgis

E2DC543D-1067-4233-9BCA-B19A69B578A4.jpeg

My Story

በሻ/ቃ ዳዊት ወ/ጊወርጊስ

የአማራ ሕዝባዊ ግንባር የውጭ ድጋፍ ሰጪ ግብረ ሀይልን እዚህ ለማድረስ ቁልፍ ሚና በመጫወቴ ደስተኝ ነኝ:: ይህንን እድል ለሰጠኝ ወደር ለሌለው ጀግና እስክንድር ነጋ ምስጋናዬን እቀርባልሁ:: ይህንን ግዙፍ ሀላፊነት ለመወጣት ከሚታወቀው በላይ ያለ እረፍት ሌት ተቀን የሰሩትን የስራ ባልደረቦቼን እደንቃለሁ:: አመሰግናለሁ:: እኔ የስራ ሰው ነኝ:: የእወቀትም ሰው ነኝ:: ታሪካዊና ትምህርታዊ የሆኑ አራት መፅሀፎችም ፅፌአለሁ:: በእንግሊዝኛም በአማርኛም::አልቀረብኝም:: ቁጥራቸው በጣም ብዙ የሆኑ ምሁራዊ ፅሁፎችን አሳትሜአለሁ::ከአውስትራሊያ አውሮፓና አሚሪካ ካናዳ የተለያዩ ሚዲያዎች ላይ ለብዙ አመታት ቀርቤአለሁ:: ፅሁፎቼም በ CNN ሳይቀር ወጥተውልኛል:: እኔ የስራ ሰው ነኝ:: የእወቀትም ሰው ነኝ:: ታሪካዊና ትምህርታዊ የሆኑ አራት መፅሀፎችም ፅፌአለሁ:: በእንግሊዝኛም በአማርኛም::አልቀረብኝም:: ቁጥራቸው በጣም ብዙ የሆኑ ምሁራዊ ፅሁፎችን አሳትሜአለሁ::ከአውስትራሊያ አውሮፓና አሚሪካ ካናዳ የተለያዩ ሚዲያዎች ላይ ለብዙ አመታት ቀርቤአለሁ:: ፅሁፎቼም በ CNN ሳይቀር ወጥተውልኛል:: አገልግሎቴን ግን የምመዝነው በተግባሬ ነው:: እውቀቴን በተግባር በማዋል የተመሰከረልኝ ነኝ:: እውቀትና ተግባርን በማያያዝ በውትድርና ሙያ፣ በኤርትራ አስተዳዳሪነት፣ በዲፕሎማሲ፣ በተባበሩት መንግስታትና ለተለያዪ መንግስታት በችሎታ አማካሪ ሆኜ አገልግያለሁ:: ሰውም የሚያውቀኝ : እኔም እራሴን የማውቀው እንደ ተግባር ሰው ነው::እውቀቴን ለተግባሬ መሳሪያ እድርጌ የኖርኩ ከጦርሜዳ እስክ ህይወት ማዳን ታላላቅ ዘመቻዎች (humanitarian operations) በእውቀትና በኩራት ያገለግልኩ ነኝ:: ለኢትዮጵያ አንድነትና ለአገሬ ህዝብ ፍቅሬን በደሜ አስመክሬአለሁ:: በውጊያ ቆስያለሁ:: አድር ባይ ሆኜ በደርግ የፖለቲካ ሥርዓት መቆየት ስችል ከሥርዓቱ መራቅ ብቻ ሳይሆን ወጥቼ ስርአቱን ለማስለወጥ ረዥምና ውስብስብ ትግል ውስጥ የነበርኩ ነኝ:: ለዚሁ ትግል በሱዳንና በኬንያ ጠረፎች አድርገን አንዳንድ ሁኔታዎችን ለማስተባበር አገር ቤት በድብቅ በእግር ገብቻለሁ:: በጊዜው እድሜዬም ትንሽ አልነበረም:: ደርግ ስሜን ለማጥፋት ያደረገውን ዘመቻ በህግ ሀሰት መሆኑን እስመስክሬአለሁ:: በአንድ ህይወት ይህንን ያህል የሥራ ውጤት ያካበተ ብዙም ሰው አይገኝምብል ማጋነን አይሆንብኝም። ለዚህም እግዚአብሄርን ከማመስገን አላቋርጥም::ለእዚህ ነው የመጨረሻውን መፅሀፌን “What a Life” ያልኩት:: ብዙ ድካምና ጊዜ የወሰደ መፅሀፍ ነው:: የሶስቱም መፅሀፎች ሽያጭ ለበጎ ስራ የተሰጡ ናቸው:: ማሳተሚያውን በግሌ ነው የከፈልኩት:: የመጨረሻው ግን በአስተዋፅኦ ነው የተከፈለው:: አማራ ሲጎዳ፣ የዘር ማጥፋት ወንጀል ሲፈፅምበት ከጎኑ ቆሜአለሁኝ:: አብይንና የወንጀሉ እስፈፃሚዎችን በኢንተርናሽናል ፍርድ ቤት ለማቅረብ ሌሎች ስራዎቼን እቁሜ ለሁለት አመት በጎደኞቼ ድጋፍ ጥናቱን አጠናቀን ለፍርድ ቤት አቅርበናል:: የኢንተርናሽናል ፖለቲካ መሰናክል እጋጥሞን አብይ አህመድ ፍርድ ቤት ገና አልቀረበም:: ከዚያም በሁዋላ ብዙ ወንጀሎች ስለ ተፈፅሙ ተጭማሪ ስራዋች ይጠይቃል:: በጊዜው ከነበረችው የፍርድ ቤቱ አቃቤ ሕግ ( ICC prosecutor general) ጋር ለዚህ ጉዳይ በቀጥታ የተገናኘ ሌላ ኢትዮጵያዊ አላውቅም:: ከእኔ ጋር በቀጥታ ተፃፅፈናል:: በእሷ ሥር ከነበሩ የህግ አዋቂዋችና የክፍል ሃላፊዋች ጋር ክሱን በተመለከተ ፕሮፌሽናል ውይይት እድርገናል:: ጥናቱም ሆነ ለዚህ ጥረት ተብሎ የተሰበሰበው ገንዘብ በቤተ ክህነቱ አካውንት ይገኛል:: ዛሬም ከእስክንድር ሌላ ጥሪ ሲመጣብኝ ስራዬን ሙሉ ለሙሉ አቁሜ ተቀላቅየዋለሁኝ:: ራሴን ጡረታ ካስወጣሁ በሁዋላ The Africa Institute for Strategic and Security Studies (AISSS) www. http://aisss.org አፍሪካ ምድር አቋቁሜ የድርጅቱ ዋና ስራ እስኪያጅ ሆኜ በመስራት ያለሁበትን ትቼ አለክፍያ ሙሉ ለሙሉ ጊዜዬን ለፋኖ ትግል ስጥቻለሁ:: የፋኖ እንቅስቃሴ ከተጀመረ በሁዋላ በአለም ደረጃ ትግላችን እንዲታወቅ የተደረገው ከግንባሩ ምስረታ በሁዋላ ነው::በኢንትርሽናል ደረጃ በአውሮፖና በአሜሪካ በአፍሪካ ( በዲፕሎማሲ ዘርፍ) በይፋ ከተነገሩት ሌላ በግንባሩ ስም እኔ የፈፅምኳቸው ጊዜው ሲደርስ ይገለፃሉ:: በአስራ ስባት አመቴ ወታደርነት የታጨሁ: ሶስት አመት ከታወቀው የቀኃስ ወታደራዊ አካዳሚ የሰለጠንኩ: አንድ አመት አሜሪካን አገር 10 ወር ሌላም ቦታ ለጥቂት ወራት ተጨማሪ ልዩ ስልጠና የፈፅምኩ ኩሩ ወታደር ነኝ:: አራት አመት ቀኃስ ዪኒቨርስቲ: (LLB) ከዚያ ሁለት ዓመት ኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ ( JD – Doctor of Jurisprudence) ቀጥሎ SMU ቴክሳስ ለPhD ቆይቼ የእናት አገር ጥሪን ተቀብዬ በደርግ ጊዜ አገሬ ተመልሻለሁ::ከዚህም በላይ በሶስት ታላላቅ ዩኒቨርሲቲዋች ( Princeton, Universty of Cape Town,Boston University, African Studies Center) በተለያዩ ጊዚያት Visting Scholar ሆኜ ተስይሜ ምርምር ስራዎች ውስጥ ተሳትፌአለሁኝ:: እንደ ዛሬው ሳይሆን በቀድሞ አባቶቻችን አርበኝነት ስሜትና ሥነስርአት ተኮትኩቼ እዚህ የደረስኩ: የዘመኑ ትምህርትና ምቾት ያልለወጠኝ ኩሩ ልበ ሙሉ ኢትዯጵያዊ ነኝ:: የእኔ አማራነት፣ የእኔ እስተዋፅኦ፣ የእኔ ኢትዮጵያዊነት በጥቂት የሴራ ፓለቲከኞች፣ ቡድንተኞችና ምቀኞች የሚተች አይደለም:: በጠባብ እውቀት: እዚህ ግባ በማይባል ልምድ: ወይንም አለምንም ልምድ: ድንበር በዘለለ ምቀኝነት: የእኔን ምንነትና ማንነት ማንቋሸሽ ጊዜው እልፎአል:: ህይወቴ ሲፈተሽ ኖሮአል:: ምክትል ሚኒስትር፣ በሚኒስትር ደረጃ ኮሚሽነር፣ የኤርትራ ክፍለሀገር ዋና ተጠሪ የነበርኩ፤ ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት በሁዋላ ያልታየ ታላቅ ኢንተርናሽናል የረሀብ ዘመቻ የመራሁ፣ በብዙ አለም አቀፍ ፅሁፎችና መድረኮች የተጠቀስኩ፣ ከብዙ መንግስታት መሪዋች ጋር በልኡካን መሪነት ቀጥሎም ከ25 ዓመት በላይ በኢንተርናሽናል አማካሪነት አፍሪካ የስራሁ፣ ለመሪዎች ጥናት ያቀረብኩ፣ ከታላላቅ ስዎች ጋር የተወያየሁ፣ ብዙ የተመስገንኩና የተከበርኩ ሰው ነኝ:: አማራን ለማደራጀትና ማህበራቱ በአንድ ጃንጥላ ስር ሆነው እንዲታገሉ የዛሬ ስምንት ዓመትና ከዚያም በሁዋላ ከቅርብ የትግል ወዳጆቼ ጋር ( አቶ ሃይለ ገብርኤል እስረስና ፕሮፌስር ጌታቸው በጋሻው) ብዙ እልህ አስጨራሽ ስብስባዎች መርቻለሁ:: በመጨረሻም “አንድ አማራ” የሚለውን ድርጅት አዋልደናል:: አብይ ስልጣን ላይ ሲወጣ ድርጅቱ ከሰመ:: አሁን ያለው “አንድ አማራ” ከቀድሞው ጋር የተያያዘ አይደለም:: ታሪኬን ብትጠመዝዙት፣ ያልኩትን ያላልኩትን እንደሚመች እየተረጎማችሁ ለራሳችሁ ቦታ ለማመቻቸት የምትፈልጉ ሁሉ በራሳችሁ ችሎታና መስዋእትነት ተፈረጁ እንጂ በእኔ ትከሻ ላይ ለመረማመድ እትሞክሩ:: ስለእኔ ምስክርነት የተፃፈውን፣ የተነገርውን፣ ወይም ጠቅላላ አስተዋፅኦዬን በቅርብ እያወቁ የማይናገሩ ብዙዎች ናቸው:: እኔን ማመስገን እነሱን ማሳነስ ይመስላቸዋልና:: የማያውቁት ደግሞ እንደትናንት ጎደኞቻቸው ስለሚያዩኝ እንደፈለጉ ያብጠለጥሉኛል:: ለእድሜ እንኳን ክብር የላቸውም:: ለማወቅም ለመጠየቅም አይሞክሩም:: ከእናንተ ጋር እልተወዳደርኩም:: ልምዳችን፣ እውቀታችን፣ አስተዋኦዋችን፣ ስነስርአታችን በጣም የተራራቀ ነው:: በጡረታ ጊዜ ጥሪ ተቀብዬ የመጣሁ ነኝ:: ጊዜዬ ውስን ነው:: እግዜር ቀናውን መንገድ ያሳያችሁ:: ባለቀ ሳዓት እስክንድርና ድርጅቱን ለማፍረስ ስሙንም ለማጠልሽት የሚካሄደው ዘመቻ አለምክንያት አይደለም:: ከጀርባው ሌላ ተንኮል ከሌለው በስተቀር በቅንነት የተነገረ ትችት ነው ብሎ ለመረዳት አስቸጋሪ ነው:: ዛሬ አማራው ድል አፋፍ ባለበት ወቅት እስክንድር ለፋኖ አስተባባሪነት አይመጥንም ማለት አማራ ነኝ የሚል ሁሉ ሊያወግዘው ይገባል:: ድል አፋፍ ያደረስን አንድነታችን ነው:: ጠላት ሊያጠቃ የሚፈልገው ይህንን ጥንካሬአችንን ነው:: ስንት ተፃፈ? ለዘመናት ስንት ውይይት ተደረገ? የስንት ሰው ህይወት ተፈተሽ? ከዚያ ዘመን በሁዋላ ዛሬ ፋኖ ወደወሳኙ የትግል ምእራፍ ሲያሽጋግረን ተናጋሪዎች፣ ፀሀፊዎች፣ አንደበታቸውንና እውቀታቸውን ከሜዳ ትግል ጋር ማገናኘት ባቃታቸው ወቅት: ብቅ ያለው እስክንድር ብቻ ነው:: እኛ ነን የበለጠ የምንመጥነው ካሉ ከሞቀ የአሜሪካ መኖሪያቸውና ቤታቸው ወጥተው ለምንድነው በረሀ እንደእስክንድር የማይገቡት? እስክንድር ቦታውን ይለቅላቸዋል። ተራ ፋኖ ሆኖ ያገለግላል:: አንመጥናለን የሚሉ ሁሉ ይውጡ! ይዝመቱ!! ወይም አርፈው ይቀመጡ:: በስንት መከራ የተገኘውን እንድነት አይከፋፍሉ::ምን ዓይነት እውቀትና አመለካከት ነው በእስክንድር የሚያስቀና? ማን ነው ከዲያስፓራ መካከል እስክንድር ጫፍ የሚደርስ? በውጭም በውስጥም ትግሉን አስተዋውቆና አስተባብሮ መሸጋገሪያው ሊያደርስን የሚችል የመሪነት፣ የአስተባባሪነት ምግባርና ተአማኒነት ያለው ባለንበት ወቅት እስክንድር ብቻ ነው:: መአድ ሲመሠረት እስክንድር መስራች አባል ነበር.:: ከዚያም በፊት ሆነ በሁዋላ የተመዘገበ ታሪኩ እንድሚያሳየው እስክንድር ለአማራ ትግል መስዋእትነት ሲከፍል የቆየው የዛሬ ተቺዎች የትግል ሜዳ ላይ ፈጽሞ ባልነበሩበት ጊዜ ነው። ዛሬ ፋኖ የብአዲንን መዋቅር በጣጥሶና የፋሽስቱ የኦሮሙማንና አውዳሚ ሃይል ደቁሶ ወደ አዲስ አበባ እየተቃረበ ሲሄድ ስልጣን የሸተታቸው ሁሉ ከየጓዳቸው በመውጣት የአማራን የህልውና ትግል ለመጥለፍና ለማደናቀፍ ብዙ የድል አጥቢያ አርበኞች አሰፍስፋችኋል። ትእግሥት ይኑራችሁ! በሚገነባው አዲስ የፖለቲካ ሥርአት ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ስለሚኖር ስልጣን ፈላጊዎች ዕድላችሁን ለመሞከር ለዚያ ጊዜ ተዘጋጁ! እዚያ ለመድረስ ግን ዛሬ በአንድነት መታገል አማራጭ የለውም:: ከሌሎች ጀግና የፋኖ አመራሮች ጋር ሆኖ እዚያ ሊያደርስን የሚችለውን እስክንድር ነጋን ለማስናከል መሞከር ግን ትግሉን አሳልፎ ለጠላት መስጠት ማለት ነው:: ከጠላት ጋር መሰለፍ ማለት ነው። አሁን ካለንበት ተነስተን ታላቁ ግባችን ላይ ያተኮረ ሥራ ለመሥራት ሙያ፣ እውቀት፣ ቅንነት፣ ትክክለኛ የፖለቲካ አቋም ያላቸው ታጋዮችን በየዘርፋ በአስቸኳይ ማሰማራት ለወሳኙ የትግል ምእራፍ አማራጭ የለውም:: ከዚህ ወዲያ ያለው ትግል ሙሉ ለሙሉ ታላቁ ሰዕል ላይ ማለትም አራት ኪሎ ላይ ያተኮረ መሆን አለበት። ምንም ይሉኝታ፣ ፍርሀት፣ ጥርጣሬ፣ መከፋፈል የሌለበት ቁርጠኛ ትግል መሆን አለበት:: ትኩረታችን በአማራው ላይ የዘር የማጥፋት፣ የማፈናቀል፣ ቤተእምነቶቻችንንና ታሪካዊ ቅርሶቻችንን የማፍረስ ወንጀል በፈጸሙብን ላይ መሆን አለበት። የአማራ እናቶችንና ሴት ልጆችን በደፈሩት ላይ መሆን አለበት። እርስታችንን በማስመለስ ላይ መሆን አለበት። ለዘለቄታው የአማራን ሕልውና በማረጋገጥ ላይ መሆን አለበት። ትኩረታችን ከላይ የተጠቀሱትንና ሌሎች ወንጀሎችን በአማራው ላይ የፈጸሙትንና ያስፈጸሙትን ሁሉ ለፍርድ በማቅረብ ላይ መሆን አለበት። በእነዚህ ዓላማዎችና በፋኖ መሀከል ገብቶ በእዚህ ያለቀ ሰዓት ሌላ ከፋፋይ እጀንዳ የሚያሲይዙ ላይ ጥብቅ ውግዘት መፈፀም አለበት:: በ120 ሚሊዮን ህዝብ ጉዳይ ላይ ጥቂት ግለስቦች ኢምንት ናቸው:: ግን ከኋላቸው እነማን ተስልፈዋል ብሎ መጠየቅም ተገቢ ነው። ሁሉም ለራሱ ሲል ይጣፍጥ:: የፋኖን ቁርጠኛነት ምንም ሀይል አያቆመውም! ቢሆንም ጥቂቶች የሚያስተናግዱት አጀንዳ ግን በሜዳ ላይ የማያስፈልግ መስዋእትነት ሊያስከፍልና የአማራን ስቆቃ ሊያራዝም እንደሚችል መርሳት የለብንም:: ስለሆነም በአይቀሬው የፋኖ ድል ማግስት እነዚህ የሞት ነጋዴዎች የመጀመሪያ ተጠያቂዎች ይሆናሉ:: ድል ለአማራ ህዝብ !!! መነሻችን የአማራ ሕልውና! መድረሻችን የኢትዮጵያ አንድነት!

Ethiopia needs a new constitution: Dawit Wolde Giorgis

January 21, 2019

Major Dawit.JPG

Major Dawit Wolde Giorgis, currently head of the Namibia-based the Africa Institute for Strategic and Security Studies, called into question the Ethiopian constitution that redefined citizenship, politics on ethnic grounds from 1991 onwards. Speaking on January 6th in Addis Ababa’s Nexus Hotel before an audience sponsored by the Vision Ethiopia, an independent network of Ethiopian scholars and professionals, Dawit Wolde Giorgis, 71, said the country is passing through a period of acute national misgiving and lasting solutions to the ongoing conflict and insecurity will not be possible while keeping the constitutional arrangements.

bottom of page