top of page

አማራውን በስልታዊ መንገዶች የማራቆት ሴራዎች እና ኢኮኖሚያዊ ጄኖሳይድ !!(ክፍል-2)

ጥቅምት 15፡ 2013 ዓ.ም ናዝሬት ከተማ የተደረገ የኦሮሙማ ልሒቃን ውይይት የ88 የአማራ ባለሀብቶችን ዝርዝር በማውጣት ባለሀብቶቹን "በተለያየ ምክንያት ሀብታቸውን ከእጃቸው መውሰድና ማደኸየት" ይገባል ሲል እንደሚከተለው አስቀምጧል።


" ከባንክ ብድር የሚወስዱበትን ማሳጣት፣ እና በነሱ ቦታ የኛ ባለሀብቶችን ብድር እንድያገኙ ማድረግ፣ ይህ ከሆነ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ በእጃችን አስገባን ማለት ነው። ከባንክ የወሰዱትን ብድር በአስቸኳይ በጉልበትም እንዲመልሱ ማድረግና ካልመለሱ ሀብታቸውን ኮላተራል ስላስያዙ በዚህ ምክንየት መውረስ። በግብር ምክንያት አዙረን ኦዲት ማድረግ፣ በተለያየ ብሮክራሲ ብድር እንዳያገኙ ማድረግ፣ ከሁሉም የፌዴራል መስሪያ ቤቶች አገልግሎት እንዳያገኙ መከልከል።

የተለያዩ ክፍያዎችን መጠየቅ፣ የተመረጡ ስራዎች ላይ ፍቃድ መከልከል፣ ያላቸውን ፍቃድም በተለያየ ምክንያት መውረስ፣ የመኪናዎቻቸውን ጉዞ መረበሽ፣ በወንጀል ምክንያት ማሰር ፣ ሀብታቸውን በተለያየ ምክንያት መውረስ፣ አዲስ አበባ ውስጥ እና በኦሮምያ ክልል ያላቸውን ቤት ሁሉ በወንጀል ምክንያት ከእጃቸው መንጠቅ። " ይላል።


የአማራውን ባለሀብት ለማጥፋት ይሔንን ያሕል የሚያሴረው የኦሮሙማ ፋሽስት ስብስብ ፡ በራሳቸው በኩል ግን ትልቅ ለውጥ እያመጡ እንደሆነ እንዲህ ሲል ይገልፃል።


"እስካሁን የሰራነው ስራ በጣም ጥሩ ነው። ከተሰሩት ስራዎች ለመጥቀስ ከተፈለገ፤ የኦሮሞ ነጋዴዎች በሚፈልጉት መልኩ የሀገሪቱ የንግድ ስርአት አመቻችተናል። የባንክ ብድር እንዲያገኙም አሰተካክለናል። ይህን በኢትዮጵያ ፖለቲካ ትልቅ ድርሻ እንዳለን ማሳያ ነው። ግን ይህ ብቻ በቂ አይደለም ማህበረሰባችን አሁንም እገዛው አስፈላጊ ነው። እኛ ቄሮዎቻችንንም እያሳተፍን ነው። የስራ እድልም እየተፈጠረላቸው ነው። ከባንክ ብድር እንድያገኙም እያመቻቸን ነው። የሚፈልጉትን መሬትም እየሰጠን ነው። ይህ እየተሰራ ነው ወደፊትም ይሰራል። ከኛ የሚጠበቀው ምን መሰለህ? መወያየት መደማመጥ ነው፥ እናንተ ደሞ በጥንካሬ መስራት ነው። እንደዚህ ካደረግን የምንፈልገውን በአጭር ጊዜ ውስጥ መፍትሄ ማምጣት እንችላለን። " ይላል።


ስልጣን የተቆጣጠረው ዘረኛ ልሒቅ ስርዓታዊ እና ስልታዊ የሌሎች ባለሀብቶችን የማደኽየት አሠራር መልከ-ብዙ ነው። የወቅቱ የኢትዮጵያ ገዢ ቡድን፡ የሌሎች ብሔሮችን ባለሀብቶች የማደኽየት "ኢኮኖሚያዊ ዘር አጥፊነት" ስልታዊ ባሕሪው ሰፊና ረቂቅ ነው።


ይሔ ስልት ⁽⁽ሌሎችን ጥሎ የመቆም፣ ነጥቆ የመክበር ስትራቴጂ⁾⁾ ነው።

አንደኛው ስልት ፡ የመንግስትን ፕሮጀክት "በሌሎች ባለሀብቶች ገንዘብ ማሠራት" ነው።

አብይ አሕመድ፥ "ገበታ ለሀገር" እያለ ራሱን በሀሳብ አመንጪነት እና የፕሮጀክት ፈፃሚነት የሚያንቆለጳጵስበት የፓርክ ልማት በባለሀብቶች በተለይም በአማራ ባለሀብቶች እና በኢትዮጵያውያን ሀብት በሆኑ ተቋማት መዋጮ የሚሠሩ ናቸው።

ገና ሲጀምረው ለአንድ የገቢ ማሰባሰቢያ የእራት ዝግጅት 5 ሚሊዮን ጥሬ ብር ክፈሉ" በማለት ባለሀብቱ ገንዘቡን እንዲያፈስ ተደርጓል። በዚህ አካሔድ እስከዛሬ ከ30- 40 ሚሊዮን ብር በግላቸውና በድርጅታቸው ያዋጡ የአማራ ባለሀብቶች አሉ።

በቅርቡ እንኳ አብይ አሕመድ "ፅፌዋለሁ" ያለውን መፅሐፍ እስከ 10 ሚሊዮን ብር አውጥተው እንዲገዙ የተደረጉ የአማራ ባለሀብቶች አሉ።

በዚሁ ስልታዊ ነጥቆ የማደኽየት መንገድ፣ ከአብይ አሕመድ ፍላጎቶች በተጨማሪ ፥ ሚስቱ ዝናሽ ታያቸው ፣ አዳነች አበቤ እና ሾመልስ አብዲሳም በየበኩላቸው ባለሀብቱን የሚያራቁቱ ስልቶችን በማምጣት የገንዘብ ገፈፋዎችን ያከናውናሉ። የአብይ አሕመድ የልጆቹ እናት ዝናሽ ታያቸው፣ በቀዳማዊ እመቤት ፅ/ቤት በኩል አስገነባለሁ በምትላቸው ትምህርት ቤቶች እና ዳቦ ቤቶች ግንባታ ውስጥ የባለሀብቶችን ኪስ መቦጥቦጦ እና ለራሷ ምስጋናን መቸርቸር ከባሏና ከኦሮሙማ መሪዎች የወሰደችው ልምድ ሆኗል።

ባለሀብት እንዲገነባ የሚደረገውን ዳቦ ቤት የቀዳማዊት እመቤት ፅ/ቤት የሠራው አድርጎ የምስጋና ኪራይ መሰብሰብ የተለመደ ነው።

ኦሮሚያ ክልል ውስጥ ፕሮጀክት ያላቸው ባለሀብቶች ሁሉ የክልሉን ፕርጀክቶች እንዲደግፉ ይገደዳሉ። ኦሮሚያ ክልል 100 የሚጠጉ ስፔሻል እና የአዳሪ ተማሪ፡ ትምህርት ቤቶችን ሲገነቡ ገንዘብ መዋጮ ጥያቄዎች ለአማራ ባለሀብቶች ሁሉ ቀርበዋል። ለቡራዩ ልዩ ትምህርት ቤት ብቻ እስከ 3 ሚሊዮን ብር እንዲያዋጡ የተደረጉ የአማራ ባለሀብቶች አሉ።

አማራ ክልል ግን ፣ ይቅርና አዳሪ ትምህርት ቤት እና ስፔሻል ትምህርት ቤት የዳስ ትምህርት ቤቶችን መልክ መቀየር የተዓምር ያሕል የሚታይ ነው።

አዳነች አበቤ ደግሞ ፡ በአዲስ አበባ ውስጥ የባለሀብቱን ኪስ መተማመኛ ያደረጉ ፕሮጀክቶችን ማወጅ እና ፡ ሠራተኛ መስሎ መገኘት ተዋህዷታል። አብይ አሕመድ ፡ "ድሃ ቀላቢ መንግስት ነን" በማለት ያሞካሸው በአዲስአበባ ያለ የምገባ ማዕከላት ግንባታ እና የምግብ አቅርቦት በባለሀብቱ ትከሻ ላይ እንዲወድቅ የተደረገ ጉዳይ ነው።

"ማዕድ ማጋራት" እና "የድሃ ቤት እድሳት" በሚል የሥርዓቱ ቁንጮ ፋሽስቶች ለሰው አሳቢ መስለው የሚተውኑባቸው ሥራዎች በሙሉ ፡ "ሀብታችንን ይዟል" የሚሉትን ማሕበረሰብ ለማደኽየት የነደፏቸው ስልቶቻቸው ናቸው።

ሌላው ይቅርና በአዳነች አበቤ በኩል ቃል የሚገቡ የእርዳታ ድጋፍ ገንዘቦች በሙሉ ባለሀብቱ እና የከተማው ደሃ ነዋሪ እንዲያዋጣ የሚደረጉ ናቸው። ከቦረና አመት ስከ ኢሬቻ በዓል መዋጮ በየሠፈሩና በየትምህርት ቤቱ የከተማው ነዋሪና አነስተኛ ንግድ ቤቶች በግዴታ ውዴታ እንዲያዋጡት የሚዴግ የገፈፋ እና ስልታዊ ማደኽየት ሥራዎች ናቸው። በቅርቡ እንኳ ለትግራይ ክልል የ500 ሚሊዮን ብር እርዳታ አደርጋለሁ ያለችው አዳነች አቤቤ የመዋዕለ ሕፃናት ተማሪዎች ሳይቀሩ ገንዘብ አዋጥተው እንዲሠጡ ለከተማው ነዋሪና ነጋዴ ትዕዛዝ አስተላልፋ በማሰባሰብ ወስዳ ሰጥታለች፣ ለትግራይ አሳቢ መስላ ፖለቲካዊ ሸቀጥ ሸምታበታለች።

በተመሳሳይ "የእኛ ነች እንወስዳታለን" ብለው ግፍ እየፈፀሙባት ባለችው አዲስ አበባ ከተማ የማስዋብ እና የከተማ ማስጌጥ ፕሮጀክቶች ሁሉ የፈረደባቸው ባለሀብቶች አደባባዮችን እና አካፋይ መንገዶችን በመውሰድ እንዲያለሙ በማድረግ የሚፈፀም ነው።

የእነ'አዳነች ሥራ በምርቃት ቀን እየተገኙ የልማት አርበኛ እና የሕዝብ አሳቢ መስሎ ምስጋናውን በመሸመት ፖለቲካዊ ሸፍጥ መፈፀም ነው።

በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ የባለሀብቱን እና የነዋሪውን ገንዘብ መጠቀም እና ማስወጣት የአገዛዙ ዘረኛ ልሒቅ ⁽⁽ሌሎችን ጥሎ የመቆም፣ ነጥቆ የመክበር ስትራቴጂ⁾⁾ ነው። ኢኮኖሚያዊ ዘር ማጥፋት በሌላ ስልት ሲገለፅ እንዲህ ነው።

ሌላኛውን የስልታዊ ማደኽየትና ኢኮኖሚያዊ ዘር ማጥፋት ሥራ እንመልከት።

ለሁለት አመታት በትግራዩ ጦረኛ ኃይል ወያኔ እና በኢትዮጵያ መካከል የተካሔደው ጦርነት ከያዛቸው ሰፊ ታሳቢዎች መካከል ፣ የኦሮሞ ልሒቃን ተገዳዳሪ አድርገው የሚያስቧቸውን አማራ እና ትግሬ ወይንም የሰሜን ኃይሎች በጦርነት ማድቀቅ አንዱ ያሳካው ግቡ ነው።

ያ ጦርነት የኢኮኖሚ ጄኖሳይድ እሳቤ ለያዘው የኦሮሞ ልሒቅ ድርብርብ ድሎች እንዳመጣ የሚታሰብ ነው። በሁለቱ ክልል ከፍተኛ የመሠረተ ልማት ውድመት ደርሷል፣ ከፍተኛ ሀብት ለጦርነት እንዲውል ተደርጓል። የአማራ አርሶአደር በሬ እና ሌሎች የቤት እንስተሳቱን ለሠራዊቱ ገብሯል።

የአማራ ባለሀብቶች በነፍስወከፍ እስከ 60 ሚሊዮን ብር ለጦርነቱ አዋጥተዋል። ምክንያቱም ሴረኞቹ ገዢዎች የአገር ማዳን ዘመቻ ፣ የሕልውና ጦርነት ብለዋልና የሚቆጠብ ገንዘብ አልነበረም። በዚያ ላይ ያለቀው ሕዝብ በፋሽስቶቹ በኩል ተገዳዳሪን የሚያዳክም ተደርጎ እንደመልካም እድል የሚቆጠር ነው።

በዚያ ጦርነት የደረሰው ውድመት ስልታዊውን የኢኮኖሚ ጄኖሳይድ የሚያረጋግጥ ነው። ከአማራ ክልል የተገኙ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በጦርነቱ የደረሰውን ውድመት መልሶ ግንባታ ለማከናወን 522 ቢሊዮን ብር ያስፈልጋል። ይሔ ግማሽ ትሪሊዮን ብር ከክልሉ የአስር አመት በጀት ጋር ተቀራራቢ ነው። ገንዘቡ የሚገኝበት እድልም አማራጭም የለም። በዚያ ጦርነት የተነሳ 11.4 ሚሊዮን የአማራ ሕዝብ ኢኮኖሚያዊና ማሕበራዊ ጫና ደርሶበታል።

ይሔ ሲሆን ነው እነሽመልስ አብዲሳ፡ ⁽⁽ኦሮሚያ ከልክ በላይ እየለማች ነው፣ ሌሎች ከልክ በላይ እየተጎዱ ነው⁾⁾ የሚያስብላቸው። ምክንያቱም አላማቸው ጥሎ ማለፍ ነው፣ ምክንያቱም እሳቤያቸው ሌላውን አጥፍቶ መቆም ነው። ስለሆነም ሌሎችን በኢኮኖሚያዊ ማሕበራዊ ቀውስ እያደኸዩ ፣ ኢትዮጵያን መዝረፍ ስልት አድርገው ይዘውታል።

የአማራን ሕዝብ በተፈናቃዮች እና ሰብዓዊ ቀውስ አዙሪት መወጠርም የኢኮኖሚያዊ ዘር ማጥፋቱ ሌላ መልክ ነው።

በዚህ ወቅት አማራ ክልል ውስጥ ከኦሮሚያና የተለያዩ አካባቢዎች የተፈናቀለ እና በተለያዩ ጣቢያዎች የተሰበሰበ 2.4 ሚሊዮን ሕዝብ አማራ አለ። ከዚህ ውስጥ 1.1 ሚሊዮን ሕዝብ አስቸኳይ የእለት ደራሽ እርዳታ የሚፈልግ የክልሉ ነዋሪ ነው። ይሔን መመገብና መንከባከብ የአማራ ሕዝብ ኃላፊነት ሆኗል። ይሔን የሚያሕል ሕዝብ ከምርት ውጭ ሆኗል። የሰው እጅ ጠባቂ ሆኗል።


ይሔ ነው ስልታዊ የኢኮኖሚ ጄኖሳይድ!!


በተጨማሪም ከኦሮሚያ እና አዲስአበባ አማራን የማፈናቀል ስርዓታዊ ስልቶች እና ዘር ማፅዳት እየተፈፀመ ይገኛል። የአገዛዙ መከላከያ ሠራዊት በክልሉ በከፈተው ጦርነት ተጨማሪ ሰብዓዊ እና ኢኮኖሚያዊ ውድመት እየተፈፀመ ይገኛል። የሁለት አመቱን ጦርነት በመሸከም እና ሠራዊቱን በመቀለብ ለዛለ ማሕበረሰብ አዲስ ጦርነት ለመውሰድ የኦሮሞ ልሒቅን ዘር አጥፊ አመለካከትና አላማ መላበስ ይጠይቃል።

ተገዳዳሪ የሚሉትን አማራ የማጥፋት ሁለንተናዊ አካሔድ፡ የኢኮኖሚያዊ ጥቃት ገፅታው በዚህ አያበቃም። ሰበቦች እየፈጠሩ ተገዳዳሪ የሚባሉ ባለሀብቶችን መበዝበዝ ብቻ ሳይሆን ከኢኮኖሚው እና ከስራ ማፈናቀል አንዱ ስልት ነው።

የአማራ ባለሀብቶችን እንዴት ከሥራ ከኢኮኖሚ እንደሚያፈናቅሉ በናዝሬት የመከሩት የኦሮሞ ልሒቃን ትልቁን የኢኮኖሚ ዘር ማጥፋት አላማ ለማስፈፀም የሚያስችል ባለሀብቶቹን የማግለልና የማጥፋት ስልት ከነደፉ ቆይተዋል። በአገዛዙ መከሰሳቸው እና መታገዳቸው የሚጠበቅ ጥቃት ነበር። ጋዜጠኛ መሣይ መኮንን የአማራ ባለሀብቶችን ክስ ሲሠማ ያስታወሰን ከጀነራሉ ጋር ያደረገው ውይይት ሰበብ ተፈልጎ ወደሥራ እንደተገባ አስታውሶናል።

"ባለፈው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ላይ መንግስት የጥፋት ሰይፉን የመዘዘ ጊዜ እንደአብሪ ጥይት የመንግስትን እርምጃ አስቀድመው የሚነግሩን የኦሮሞ ሚዲያዎች እነስታር ቢዝነስ ግሩፕን ጠቅሰው እርምጃ እንዲወስድባቸው ሲቀሰቅሱ ነበር። የተናገሯት ከመሬት ጠብ አላለችም። የሚዲያው ክንፍ አስቀድሞ ይናገራል፥ የፖለቲካው ክንፍ እርምጃውን ወስዶ ይፋ ያደርጋል። የሆነው ይኸው ነው።"ይላል መሳይ።


የአማራ ባለሀብቶቹ የባንክ ሒሳብ እገዳ ከአጠቃላዩ የኢኮኖሚ ጄኖሳይድ ታሳቢዎችና ስሌቶች ተነጥሎ የሚታይ አይደለም። ጦርነት ተሸክሞ ለከረመ ባለሀብት ብድርና ማበረታቻ ሳይሆን የገንዘብ እገዳ አዘዙበት። በጠሩት ቦታ እየተገኘ አምጣ ያሉትን ገንዘብ እየሠጠ፥ ሥራ ያሉትን እየገነባ የከረመውን ባለሀብት በጠላትነት ፈርጀውታል።


ዛሬ በአገዛዙ ሰዎች ስሌት ሕግ ተገዳዳሪን ለመጣል ሕግ ይወጣል፤ ወገን ያሉትን ለመጥቀም ሕግ ይሻራል። ለጥቅም ከበጀ ሕግ ይወጣል።

የአዲስአበባን መሬት ተቆጣጥሮታል ያሉትን ሕዝብ ለማጥቃት በተለያየ ጊዜ የእገዳ እና የመረጃ ስብሰባ ስራ ሲለዋወጥ ከርሟል። አንዴ ግዢ ሲታገድ ፡ ሌላ ጊዜ ስም ማዘዋወር ይታገዳል። አንዱ ሲፈቀድ ሌላ ይታገዳል። ሌላው ይቅርና ለረጅም ዘመን አቁመውት የኖሩትን የመሬት ሊዝ ጨረታ ከ80 በላይ የአማራ ባለሀብቶችን የባንክ ሒሳብ ካገዱ በኋላ አውጥተው አጫርተዋል።


ይሔ ሁሉ ከተማውን ለመቆጣጠር በሚደረግ ፋሽስታዊ ስሌት የሚደረግ ከንቱ ድካም ነው። በኮንስትራክሽን ዘርፍ ፣ በጉምሩክ ፣ በወጪና ገቢ ንግድ ፡ በሌሎችም "ሌሎች ተቆጣጥረውታል" ያሉትን ለመቆጣጠር የሚደረገው ደባ የተለየ ነው። ዛሬ ዝም የተባለ የሚመስለው የመርካቶ ንግድ ቁጥጥር፥ ነገ የጉራጌና ስልጤ ነጋዴ ላይ የማፅዳት ሥራ መከናወኑ የማይቀር እውነት ነው። ነገ በተራው የሚያለቅስ ብዙ ነው።

መንግስታዊ አገልግሎትን በገንዘብ የሚሠጥ ሸቀጥ ያደረገው ገዢ ቡድን ሀፍረት የለውም። አገልግሎት ፈላጊን በቋንቋ ለይቶ ገንዘብ መቀበል ከተራ ቢሮክራሲ ያለፈ ሌላን አካል የማደኽየትና ገንዘቡን የመንጠቅ ስልታዊ ፋሺዝም ነው።

የቡድኑ መሪ የሆነው አብይ አሕመድ ራሱ "ሰነድ በእግሩ አይሔድም" ይባላል በማለት ፣ አይን ያወጣውን እና በሙስና የነቀዘውን ስርዓት ማጭበርበሪያ ንግግር በማድረግ የመንግስት አገልግሎት በገንዘብ ሲሸጡ መኖራቸውን መስክሯል።


የሙስናው አይነትና አድማስ እጅግ ሰፊ ጉዳይ በመሆኑ በሌላ ጊዜ የምንመለከተው ይሆናል።


ስርዓቱ ምን ያሕል በነውረኛ ዘር አጥፊዎች እጅ እንደወደቀ ተዘርዝሮ የማያልቅ ግፎቻቸው ምስክር ናቸው። በቅርቡ እንኳ ቤት በማፍረስ ሕፃናትን ለዱር አውሬ የዳረገ ቤተሰብን ለጎዳና ልመና ያበቃ ዘር ማፅዳት ተከትሎ የአገዛዙ ካድሬ "ሕገወጥ ድሆች ነበሩ፣ ሕጋዊ ድሃ አደረግናቸው" በማለት ንቀታቸውን ግዴለሽነታቸውን እና የኢኮኖሚ ጄኖሳይድ ተግባራቸውን አሰምቷል።

የኢኮኖሚ ዘር ማፅዳት (economic cleansing) ለረጅም ጊዜ በትጋት የተሠራበት ነው። በአዲስአበባ ከሥራው የሚባረረው ፣ ሥራ እንዳይመቸው የሚደረገው ፣ ለቆ እንዲወጣ ሰበብ የሚፈለግበት ብዙ ነው።

አንዳንዶች ዛሬ "አዲስአበባ የነበሩ ጫት ነጋዴ ጉራጌዎች የት ሔዱ!?" ይላሉ። እነሱን የሚተካ የገጠር ወጣት ከኦሮሚያ አስገብተው በሚታተምና በሚዘረፍ ገንዘብ አሠማርተውታል። የጋሞ ሸማኔዎች በግፍ ተጠርገዋል። የእጅ ጋሪ እየገፉ አትክልት በመሸጥ የሚተዳደሩ በርካታ ወጣቶች ከእንጀራቸው ተነቅለዋል። በዚሁ ሥራ ላይ የነበረ የደቡብ ኢትዮጵያ ወጣት፡ "ምነው ሥራ ተዋችሁ እንዴ!?" ተብሎ ሲጠየቅ የመለሰው መልስ የሥርዓቱን ፀረ-አማራ አላማዎች ጠቋሚ ነው። ልጁ፡ "አማራዎች ይውጡና ተደራጅታችሁ ትጀምራላችሁ ብለውናል" ነው ያለው።


አማራን የመጥላትና የመፍራት ፖለቲካቸው፡ በከተማዋ ዳርቻ ተሠማርተው የሚሠሩ የባለሶስት እግር ተሽከርካሪ (ባጃጅ) ባለንብረቶችንም አልማረም። ከአስርሺህ የሚልቁትን ወጣቶች ሥራ በማስቆም በርካቶች አዲስአበባን ለቀው እንዲወጡ አድርገዋል። በሕዝብ ጩኸት እንዲቆዩ የሆኑትን አሽከርካሪዎች ደግሞ አያሌ ገደቦችን በመጣል ፡" ሒድ አትበለው እንዲሔድ አድርገው" ይሉት አይነት ክፋት እየፈፀሙ ነው።

ሰዎቹ በአንድ በኩል ለዲሞግራፊ ያግዘናል ብለው ባሰቡበት ሁሉ ሸራዎችንና ቆርቆሮዎችን እየወጠሩ ለሥራ የሚደራጁ ለሚሏቸው ያድላሉ። በሌላ በኩል ደግሞ ስንቱ ድሃ ለፍቶ የእለት እንጀራ የሚበላባቸው የሸራ ቤቶችና የመንገድ ዳርቻ ጉሊት ንግድ ቤቶችን ያፈርሳሉ።

የጉሊት ሥራ እና የቀላል ሸራ ቤት ንግዶች ለዘመናት የኖሩ ሆነው ሳለ አዲስ ግኝቶች አስመስለው "የሽብር ቡድኖች መደበቂያ ናቸው" በማለት በድሆች ጉሮሮ ላይ ተዘባበቱ።

በቅርቡ የፈረሱ ሸራቤቶችን በተመለከተ የአካል ጉዳተኞች ማህበር ባወጣው መግለጫ፣ "የሸራ ቤቶች የፈረሱት በከንቲባ አዳነች አቤቤ ትዕዛዝ ነው" በማለት የተግባሩን አሉታዊነት ገልፀዋል።


የአካል ጉዳተኛ ማህበራቱ ጨምረው እንዳሉት፡ ⁽⁽ ከሸራ ቤቶች ፅዱ የሆነ ከተማ መገንባት ስላስፈለገ ብቻ በተለያዩ ማህበራት ተደራጅተን ለንግድ የተቀበልናቸው የንግድ ቤቶቻችን ያለምንም ቅደመ ሁኔታ እንዲፈርሱ ተደርገዋል⁾⁾ ብለዋል።


ይሕ መልከ-ብዙ የኦሮሞ ገዢ ቡድን የኢኮኖሚያዊ ጀኖሳይድ እንደልብ ገንዘብ እያተሙ ለቡድናቸው በሚረጩት ገንዘብ በዋጋ ግሽበት የታመመ ኢኮኖሚ ሲፈጥር በልቶ ማደር ለከተማው ሕዝብ ጭንቅ ተደርጓል።

የዚህም አላማ የኢኮኖሚ ተሰዳጅ (economic refugees) በመፍጠር ከተማውን ጥሎ የሚወጣ ነዋሪ የመፍጠር እና አዲስአበባ ሰው የማይኖርባት ነች የሚያሰኝ የኑሮ ውድነት የሚፈጥር ውል አልባ አስተዳደር ነው።

ዛሬ በሚፈፅሙት የዘር ማፅዳት እና የዘር ማጥፋት በርካቶች ወደ ጎዳና ሕይወት እየተዳረጉ ይገኛሉ። እነዚህ ግፈኛ የአገዛዙ ሰዎች ግን በአዲስአበባ ሴተኛ አዳሪነት እና ልመና መቆም አለበት በማለት በአስገዳጅ ሕግ እየሠሩበት ነው። "መንግስትን ለመገልበጥ" እና "ተልዕኮ ያላቸው" በማለት ወደከተማው እንዳይገባ የሚያግዱትን ሕዝብ ከከተማ እንዲወጣም የሚችሉትን ሁሉ ግፍ እየፈፀሙ ነው።

የኦሮሚያ ፋሽስታዊ ቡድን አሁን በሚያስተዳድረው ግዛት ሕገወጥ ቤቶች ማፍረስ በሚል የዘር ማፅዳት እየፈፀመ ይገኛል። እሱ ብቻ ሳይሆን በክልሉ 127ሺ ሕገወጥ የንግድ ፈቃዶች አሉ በማለት በክልሉ ሌሎች ሠርቶ አዳሪዎችን የማፅዳት አላማ አስተዋውቋል። በዚህ የሚፈናቀለውን ወገን እና የሚፈሰውን እንባ ወደፊት የምንሰማው ነው።

ይሔ ሁሉ ሲፈፀም የአማራ ልሒቅና ባለስልጣን፡ በአንድ በኩል ዘር አጥፊዎችን አጅቦ ተሰልፏል። የብሔራዊ ባንክ ገዢዎቹ ቀደም ሲል ዶር ይናገር ደሴ ነበር፣ አሁን ሞሞ እስመለአለም ነው። የልማት ባንክ ፕሬዝዳንት እና ቦርድ ሰብሳቢዎችም አማራዎች ናቸው። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርም፡ የደሕንነት ተቋሙ ኃላፊም አማራ ነን የሚሉ ናቸው። በሌላ በኩል ግን ሰፊው የአማራ ሕዝብ እና ልሒቁ ድብታ እና ዝምታ ውጦት ይገኛል።

ሚድያው በአማራው ላይ የሚሠራውን ሁለንተናዊ ግፍ አደራጅቶና አጠናቅሮ ከማቅረብ ይልቅ በእለታዊ አጀንዳ ሲዋልል ይገኛል።

ዛሬም መታገል ሳይሆን የሚችለውን በማድረግ ወገኑን ከጥፋት ለማዳን ከመስራት ይልቅ ዝም ብሎ ተመልካቹ አማራ ሰፊ ነው።

ይበቃል!! የምንችለውን በተግባር እናረጋግጥ !!

0 views0 comments

Comentários


bottom of page