top of page

በኢትዮጵያ ለአሜሪካ አምባሳደር የተሰጠ ምላሽ።

የከበረ ሰላምታ ለሁላችሁም!


አሁን ስልጣን ላይ ያለው አገዛዝ ወደ ስልጣን ከመጣ እነሆ ስድስት ዓመታት አለፉ። ታዲያ፣ በእነዚህ ስድስት ዓመታት አማራዎች በብሄራቸው ምክንያት ተነጥለው ተፈርጀዋል፣ በክፉ ተጥላልተዋል፣ ተፈናቅለዋል፣ ተጠቅተዋል፣ በጅምላ ተጨፍጭፈዋል። ይህ ሁሉ የሆነው በክልል መንግስታት ብቻ ሳይሆን፣ እንደያውም በበለጠ በሚያሳስብ ደረጃ፣ በፌደራል መንግስቱ ተዋናይነት ነው።


ተመልከቱ፣ ከ 1966ቱ አብዮት ጀምሮ፣ በተለያዩ ብሄር ተኮር ድርጅቶች አማካኝነት አማራዎች በብሄራቸው ምክንያት ላለፉት ሃምሳ ዓመታት ሲጠቁ ኖረዋል። ያለፉትን ስድስት ዓመታት ለየት የሚያደርገው ነገር ፣ የዚህ ብሄር ተኮር ጥቃት ዋና ተዋናይ ራሱ አገዛዙ መሆኑ ነው።


ታዲያ፣ እኛ አማራዎች ይህንን የአገዛዙን ጥቃት

ለመከላከል ከመነሳት ውጭ ሌላ አማራጭ አልነበረንም።

ከታሪክ መማር አለብን። የዘር ፍጅትን ለመፈፀም አቅም ያለው አካል መንግስት ብቻ ነው፤ በተለይ አክራሪ ብሔርተኛ ሆነው የመንግስትን ስልጣን የያዙ ኃይሎች።


የምንታገለው እንደ ህዝብ የመኖር መብታችንን ለማስከበር ነው። የመኖር መብት ደግሞ የመብቶች ሁሉ መሰረት ነው። ለዚህ ነው ምንም እንኳን የትግላችን የመጨረሻ መቋጫው ፖለቲካ ቢሆንም፣ አሁን ያለን ትግል ከፖለቲካ በላይ የህልውና ትግል ነው እያልን አጥብቀን የምንናገረው።


ስለሆነም፣ እስከአሁን ድርድርን አስመልክቶ ስናራምደው የነበረው አቋም ባለበት የሚቆይ

ቢሆንም፣ ጥያቄው "በምን መልክ ነው?" የሚል ነው እንጂ፣ በትግሎች ሂደት ድርድር አንዱ የሂደቱ አካል እንደሆነ እንገነዘባለን።


በዚህ በኩል የአሜሪካ መንግስት የአማራን

ህዝብ የሚወክለውን ፋኖን እና አገዛዙን ለማነጋገር ሁኔታዎችን ለማመቻቸት እየሞከረ ነው። ይህ ጥረት ፍሬ ሊያፈራ የሚችለው ዋና ዋና የፋኖ አደረጃጀቶች ያቀፈ አንድ የአማራ ፋኖ ድርጅት በመጀመሪያ ሲቋቋም ነው። ይህንን ስራ ለማጠናቀቅ ትንሽ ጊዜ ያስፈልገናል። የአማራን ህዝብ ወክሎ በሙሉ ስልጣን ሊናገር የሚችለው እንዲህ ያለው ድርጅት ብቻ ነው።


የአሜሪካን መንግስት፣ ብሎም የዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ በአጠቃላይ፣ በኢትዮጵያ ውስጥ የዘር ፍጅትን (ጄኖሳይድ) ለመከላከል ስለምታደርጉት ጥረት ምስጋናችን ላቅ ያለ ነው።


ፈጣሪ ከሁላችንም ጋር ይሁን!!


እስክንድር ነጋ፣

የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ሠራዊት።

54 views0 comments

Comments


bottom of page