top of page

በኮረኔል ፈንታው ሙሃባ እና ኮረኔል ሞገስ ዘገየ ከሚመራው የፋኖ ኃይል በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የተሰጠ አስቸኳይ መግለጫ‼️

መንግሥትየእምነት ተቋማትን ለማውደም ንፁሃንን በግልፅ ለመጨፍጨፍ እንዲመቸው ህግ ማስከበር በሚል ተልካሻ ልብ ወለድ በመድረስ ሆን ብሎ በህዝባችንና በእምነት ተቋሞቻችን ላይ ግልፅ የሆነ ጦርነት በመክፈት ከፍተኛ ውድሙት በአማኞችና በእምነት ተቋሞች ላይ እያደረሰ ይገኛል።

በመሆኑምመንግሥት የራሱን ፍላጎት ፍፁም ጥላቻና እብሪት በህግ ማስከበር ስም እየተወጣና ህዝባችን ላይ ባለው ወደር የሌለው ጥላቻ በግልፅ እየገደለንና ጥላቻውንም ፊት ለፊት እያሳየን ይገኛል። ህገ ወጡና ሽብርተኛው የአብይ አህመድ መንግሥት የዘር ጨፍጫፊነቱን ህጋዊ ለማድረግ የሄደበት ርቀት ህዝብን እያታለለ የሚኖርበት ያደገበት ቀጣፊ ባህሪው እንደሆነ እኛም እንገነዘባለን ህዝባችንም ጠንቅቆ ያውቃል።

በመሆኑምአንባገነኑ የአብይ አህመድ መንግሥትና ሰራዊቱ በንፁሃን ህዝባችን ላይ እየደረሰ ባለው ሰቅጣጭ ጭፍጨፋ በእጅጉ ያዘንንና ልባችን የደማ እንደሆነ ለመግለፅ እየወደድን ጉዳትና ሞት ለደረሰባቸው ንፁሃን ጠበልተኞች የገዳም አባቶች እና በመስጊድ ውስጥ ጉዳትና ሞት እንዲሁም በንፁሃን ህዝባችን ላይ የተፈፀመባችሁን ድርጊት እያወገዝን ለቁስላችሁ ምህረትን ለሞታችሁ እረፍትን ለወዳጅ ዘመዶቻችሁ ከልብ መፅናናትን እንዲሰጥልን እንመኛለን።

እንደሚታወቀውመንግሥት እንደ ህዝብ አማራን! እንደ እምነት ተቋም የኢትዮጵያን ህዝብ ነባር እምነት የሆኑትን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስና እስልምንና ጠል መሆኑና እነርሱን ለማጥፋትም 7/24 ያለ እረፍት የሚሰራ ነውረኛ ኢትዮጵያ ጠል መንግሥታዊ ስርዓት መሆኑ ይታወቃል። ይህ የከረፋ መንግሥታዊ ስርዓት የጀመረውን ከታች የዘረዘርናቸውን አፀያፊ ተግባር በአስቸኳይ እንዲያቆም ስንል በጥብቅ እናሳስባለን።

1ኛ. በታላቁ እስክንድር ነጋና በሚመራው የአማራ ህዝባዊ ግንባር /APF ላይ የሚደረግን ስም ማጥፋትና የማሳደድ ተግባር እንዲሁም በግንባሩ መሪ እስክንድር ነጋ ላይ የታወጀውን የግድያ ትዕዛዝ የማንቀበለውና እስከ መጨረሻውም ከፅኑ ታጋያችን ጎን እንደምንቆም እየገለፅን ከግንባሩ የሚወርዱ ማናቸውንም ትእዛዝና ግዳጅ ለመፈፀም ሙሉ ፍቃደኞችና ዝግጁ መሆናችንን ጭምር ከወዲሁ እንገልጻለን።

2ኛ. በመዲናችን አዲስ አበባ በሙስሊሙ እምነት ተከታዮች የሚደረግን ጭፍጨፋና አዲስ ከተማ ለማዋለድ በሚል ፌዝ ወይም ህዝባዊ ንቀት የመስጂድ/የእምነት ተቋማት ውድመትና ማንነት ተኮር መፈናቀሎችን የምናወግዝና ከእንግዲህ የማንታገስ እንደሆነ ለማሳወቅና የትግል ቀይ መስመራችንም እንደሆነ በማወቅ ከልጅ እስከ አዋቂ ከጎናችን እንድትቆሙ ሕዝባዊ የትግል ጥሪያችንን እናቀርባለን።

3ኛ. በምስ/ጎጃም ደብር ኤሊያስ ገዳም ላይ የደረሰውን አስነዋሪ መንግሥታዊ ሽብር እያወገዝን ህዝባችን ራሱን ለማይቀርለት የሞት ሽረት ትግል ራሱን ከወዲሁ እንዲያዘጋጅ እና የተጀመረውን ሕዝባዊ ትግል አጠናክሮ እንዲቀጥልና እንዲሁም ያልተቀላቀለ ለቅድስናው ትግል ራሱን እንዲያዘጋጅና በየደረጃው ለሚደረጉ ጥሪዎች ነቅቶና ተዘጋጅቶ እንዲጠብቅ እናሳስባለን።

4ኛ. የሃገር መከላከያ ሰራዊትና የአማራ ክልል የፀጥታ ኃይሎች መንግሥት እያደረገ ባለው አፀያፊ ተግባር ባለመሳተፍ ህዝባዊነቱችሁን ከህዝብ ጎን በመቆም እንድታሳዩ ጥሪ እያቀረብን ይህን ማድረግ ያልቻለ ሰራዊት ከህዝብ የተነጠለ የፓርቲ ዘበኛ እንደሆነ አውቆ ከቻለ ከመከላከያ ሰራዊት እንዲሁም ከማናቸውም የመንግሥት ፀጥታ ተቋማት ራሱን እንዲያገልና ከህዝብ ጎን እንዲሰለፍ በህዝብ ስም ጥሪ እናቀርባለን።

በመጨረሻምአማራነቱ እንደ ወንጀል ተቆጥሮ በግለሰቦች ፍላጎት በሃሰተኛ ከሳሾች ያለምንም ፍርድ በእስር ላይ ሲንገላታ የከረመው ጓዳችን አርበኛ ዘመነ ካሴ ከእስር ተፈቶ ቤተሰቡንና የሚወደውን ህዝቡን በመቀላቀሉ የተሰማንን ልባዊ ደስታ እየገለፅንወደ ተጀመረውም ፈታኝ የትግል ጉዞ በማይናወጠው ፅኑ አቋሙ በአጭር ጊዜ በተሻለ ስነልቦናና በተሻለ የትግል መንገድ እንደሚቀላቀልና ለትግላችን ትልቅ አቅም እንዲሚሆን ኃይላችን በፅኑ ያምናል።

ኃይላችን ያለው "ፋኖ" ከሚለው ታላቁ ስማችን ላይ ነው።

ድል ለሰፊው ለአማራ እና ለኢትዮጵያ ሕዝብ!

ግንቦት 28 ቀን 2015 ዓም

0 views0 comments

Comments


bottom of page