top of page

ከአማራ ፋኖ አንድነት በወሎ ላስታ አውራጃ አሳመነው ብርጌድ የተሰጠ አስቸኳይ መግለጫ

Updated: Aug 29, 2023

በዐብይአህመድ አሊ የሚመራው የብልጽግና መንግስት በአማራ ክልል በአውሮፕላን ቀረሽ ጦርነት እየፈጸመ ባለው ወረራ፣ ግድያ እና ማፈናቀል በንፁሁ የአማራ ህዝብ እና የሀይማኖት ተቋማቱ ላይ መጠነ ሰፊ ጥፋት ፈጽሟል።

የአብይአህመድ ብልፅግና የዕለት-ተዕለት ተግባር አድርጎ በያዘው ይህ ወንጀል የጸሎት ቤቶችን በማፍረስ አማኞችን ከፈጣሪ እያለያየ ይገኛል።

በአዲስአበባ የእስልምና እምነት ተከታዮችን እንዲሁም በአማራ ክልል በኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ላይ ይቅር የማይባል ወንጀል እየፈጸመ ነው። የሐይማኖት ተቋማትን፣ የዕምነቱ ተከታዮችን በከባድ እና ቀላል መሳሪያዎች ግድያ ፈጽሟል፤ ውድመትም አስከትሏል።

ለአብነትከግንቦት 15-26/2015 ዓምድረስ በደብረ ኤልያስ ወረዳ በሚገኘው የቅድስት ሥላሴ እንድነት ገዳም ምዕምናን እና በአዲስ አበባ በአንዋር መስጅድ ሙስሊሞች ላይ የተፈጸመው ጭፍጨፋጨዎች ይጠቀሳሉ።

ይህለሚመራው ህዝብ ርህራሄ የሌለው እና የሀገር መገለጫ የሆኑ ተቋማት አውዳሚ የሆነ መንግስት በሚቆጣጠራቸው ሚዲያዎች አይናችሁን ጨፍኑ ላሞኛችሁ እያለ ሲያላዝን ይሰማል።

የአማራህዝብ የገጠመውን ዘርፈ ብዙ ችግር ለመቅረፍ በአማራነቱ ተደራጅቶ እና የአባቶችን ነፍጠኝነት ስሜት ወርሶ ህልውናውን በክንድ ለማስከበረ በጀመረው የአማራ ሕዝባዊ ግንባር እና በመሪው በጀግናው አስክንድር ነጋ ላይ "የጋራ የደህንነት ግብረ ኃይል" በማቋቋም አጽናፍ ነጠቅ ዘመቻ እያደረገ ይገኛል። የማይሰበረው ክንድ የተዘረጋ የሕዝብን ችግር ተረድቶ በጠላቶቹ ዘንድ ብርቱ በትር ለማሳረፍ መሆኑን ያልተረዳው ከሀዲው መንግስት በመሪያችን እስክንድር ነጋም ሆነ በአማራ ሕዝባዊ ግንባር ላይ የጀመረውን እንቅስቃሴ ሊገታ ይገባል ሲል የአማራ ፋኖ አንድነት በወሎ ላስታ አውራጃ አሳመነው ብርጌድ ያሳስባል።


ለመላውህዝባችን የሚከተለውን ጥሪ ያቀርባል፦


1ኛ) የአማራን ህልውና በክንዱ ለማረጋገጥ የተቋቋመውን "የአማራ ህዝባዊ ግንባርን" እና መሪው ታላቁ እስክንድር ነጋን በአገር ውስጥ እና በውጭ የምትገኙ በምትችሉት ሁሉ እንድትደግፉ፤


2ኛ) መላው ህዝባችን በሐይማኖት ተቋማት በተፈፀመው ጭፍጨፋ ለጠፋው ነፍስ እና ለወደመው ንብረት የአብይ አህመድ አሊ መንግስት ተጠያቂ እንዲያደርግ፤ በድርጊቱ ተሳታፊየሆኑ ሁሉ ለህግ እንዲቀርቡ እንሰራለን።


3) በእነዚሁ ተቋማትለጠፋው ነፍስ እና ሐብት መንግስት ካሳ እንዲከፍል፣


4ኛ) ገዳይ ለሆነው የአብይ አህመድ አገዛዝ አሸከር በመሆን በወገኖቻችሁ ላይ ምላጭ የምትስቡ የፖሊስ፣ የሚሊሻ፣ የአድማ ብተና እና የመከላከያ አባላት ከድርጊታችሁ እንድትታቀቡ ጥሪ እያቀረብን፤ ይህ ካልሆነ በራሳችሁም ሆነ በቤተሰቦቻችሁ ላይ አጸፋዊ ምላሹን ፋኖ እንደሚወስድ በጥብቅ ለማስጠንቀቅ እንወዳለን።


5ኛ) ከቀበሌ እስከ ፌደራል ያላችሁ የአማራ ወኪሎች ሕዝብ የሰጣችሉን አደራ በልታችሁ ለበሰበሰና ህዝብ ጠል ለሆነ አገዛዝ ባርነት አድራች ይቅር የማይባል ሥራ ወጥታችሁ ከሕዝብ ጎን እንድትቆሙ እንገልጻለን።


6ኛ) በአማራ ህዝባዊ ግንባር እና በመሪው ታላቁ እስክንድር ነጋ ተማምነን የአማራ ህዝብ ትግል ግብ እንዲመታ እና ሕዝባችን ማህበራዊ እረፍት አግኝቶ በኢኮኖሚው ተጠቃሚ እንዲሆን፤ በመሰረታት ሀገሩ ከበይ ተመልካች ወጥቶ የላቡን እንዲያገኝ፤ ሁሉም የፋኖ አደረጃጀቶች የትግሉ አካል እንዲሆን ጥሪ ያስተላልፋል።


የአማራ ህዝብን እና ዕሴቶችን በማጥፋት የምትገነባ ሃገር አንሻም!!!


ድል ለአማራ ሕዝብ!!


ግንቦት 28 ቀን 2015 ዓ.ም


ወሎ አማራ፤ ኢትዮጵያ

Recent Posts

See All

የምስራቅ አማራ ፋኖ የአቋም መግለጫ

ከአማራ ፋኖ አንድነት ም/ቤት በአምባገነኑአብይ አህመድ አሊ የሚመራው አማራ ጠሉ የብልጽግና መንግስት በአማራ ህዝብ ላይ ጦርነት አውጆ ዘርፈ ብዙ ውድመት እያደርሰ ይገኛል። የአማራን ህዝብ በእምነቱና በብሄሩ በዋለበት...

Comments


bottom of page