top of page

የምስራቅ አማራ ፋኖ የአቋም መግለጫ

Writer's picture: Amhara Fano People's Force (AFPF)Amhara Fano People's Force (AFPF)

ከአማራ ፋኖ አንድነት ም/ቤት


በአምባገነኑአብይ አህመድ አሊ የሚመራው አማራ ጠሉ የብልጽግና መንግስት በአማራ ህዝብ ላይ ጦርነት አውጆ ዘርፈ ብዙ ውድመት እያደርሰ ይገኛል። የአማራን ህዝብ በእምነቱና በብሄሩ በዋለበት ባደረበት ሁሉ እያሳደደ አገርም እምነትም እንዳይኖረው ለማድረግ የብልጽግና መንግስት ያለ እረፍት እየሰራ ይገኛል። ለዚህ ማሳያም የሰሞኑን የአዲስ አበባው የአንዋር መስጅዱ የህዝበ ሙስሊሙ ጭፍጨፋ እና የደብረ ኤልያሱ የቅድስተ ስላሴ አንድነት ገዳም የኦርቶዶክሳውያኑ ጅምላ ጭፍጨፋ ዋነኛ ማሳያ ነው።

ህዝብን በጅምላ መግደሉ፥ ማሳደዱ፥ ማዋከቡ እና ማፈናቀሉ በአማራው ህዝብ ላይ ይበርታ እንጅ በሁሉም ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ላይ እንደሆነ የአደባባይ ሀቅ ነው። በኦሮሙማ የሚመራው የብልጽግና መንግስት በአጠቃላይ ሰላም ፈላጊ መንግስት አይደለም። የብልጽግና መንግስት ሀገራንኢትዮጵያን ብሎም የአማራ <ክልል>ን ወደ ዘላቂ የሰላም እጦትና ቀውስ ውስጥ በማስገባት የሚፈልገውን ሀገረ መንግስት ማዋለድ መዳረሻው እንደሆነ ይታወቃል።


ስለሆነምባለፈው ሁለት ወራቶች ለሀገርና ለህዝብ ስንል እንደ ትህነግና ኦነግ ደቡብ አፍሪካ ኬንያ ወይም ታንዛኒያ ሳይሆን በሀገር በቀል እሴታችን በሆነው የሽምግልና ስርአት ከመንግስት ጋር ለሰላም ብለን ተደራድረን የነበረ መሆኑ ይታወቃል።ነገር ግን የብልጽግና መንግስት የአማራ ክልልን ሰላምና መረጋጋት ስለማይፈልገው "አታንደፋርሽብኝ" ብሎ አሁን ያለንበትን ጦርነት ከፍቶብናል።

ስለሆነምመላው የአማራ ህዝብ ሆይ የተጀመረው ትግል የፍትህ፥ የእኩልነትና የዲሞክራሲ ብቻ ሳይሆን የመኖር ያለመኖር የህልውና ትግል መሆኑን በመገንዘብ የሞት የሽረት ትግል ማደረግ እንደ ህዝብ ብቸኛ መዳኛችን መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል።

በመጨረሻምየተጀመረው የአማራ ህዝብ ትግል የህልውና ብሎም የተቀማናትን ሀገራችን ኢትዮጵያን የማስመለስና የሀገራችን ባለቤት የመሆን ነው።


የአማራ ፋኖ አንድነት ምክር ቤት የምስራቅ አማራ ፋኖ ለህዝባችን የሚከተሉትን ጥሪ ያቀርባል።


1ኛ. የአማራ ፋኖአንድነት ም/ቤት የምስራቅ አማራ ፋኖ ከነጻነት ታጋዩ እስክንድር ነጋ ጋር በአንድነት እየሰራን የነበረ ሲሆን አሁን ከተመሰረተውና በእርሱ ከሚመራው የአማራ ህዝባዊ ግንባር ጋር በጋራ የምንታገል መሆኑን ለህዝባችን ለመግለጽ እንወዳለን።

2ኛ. የአምባገነኑን ስርአት ነውር በአደባባይ በመቃወማቸው እና ከህዝብ ጎን በመቆማቸው ያለወንጀላቸው የታሰሩት የአማራተወላጅና ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞች፥ አትጊዎች፥ ሙህራኖችና ፋኖዎቻችን እንዲፈቱ ህዝባችን የጋራ ትግል እንዲያደርግ ጥሪ እናቀርባለን።

3ኛ. መላው ህዝባችን በሀይማኖት ተቋማት በተፈጸመው ጭፍጨፋ ለጠፋው ነፍስና ለወደመው ንብረት የአብይ አህመድ የብልጽግና መንግስትን ተጠያቂ እንዲያደርግና በድርጊቱ የተሳተፉ ሁሉ ለህግ እንዲቀርቡ ህዝባችን የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ስንል ጥሪ እናቀርባለን።

4ኛ. በሀይማኖት ተቋማቶቹ እና ጦርነት በተከፈተበት ቦታ ሁሉ ለጠፋው ነፍስና ለወደመው ንብረት መንግስት ካሳ እንዲከፍል እንጠይቃለን።

5ኛ. ከአማራ ህዝብ አብራክ የወጣችሁ ከቀበሌ እስከ ፌደራል ያላችሁ አመራሮች፥ፖሊሶች፥ሚሊሾችና አድማ ብተናዎች ከቻላችሁ ከህዝባችሁ ጎን ተሰልፋችሁ ይህንን ውስጡ የተፈረካከሰና የበሰበሰ ስርዐት እንድትታገሉ ጥሪ እያቀረብን ይህንን ሳታደርጉ ብትቀሩ ግን በእናንተም ሆነ በቤተሰቦቻችሁ ላይ ለሚደርስ ማንኛውም አይነት ጥቃት ሀላፊነት የማንወስድ መሆኑን ለማረጋገጥ እንወዳለን።

6ኛ. በባህር ማዶ በአሜሪካ፥በአውሮፓ፥በአረብ ሀገራቶች በአጠቃላይ በመላው ውጪው አለም የምትኖሩ የአማራ ተወላጅ ዲያስፖራዎች በጸረ-ወያኔ ትግሉ የነበራችሁ ጉልህ ሚና አሁን ላለንበት የህልውና ትግልም ይኼው የነበረው ፋኖን በትጥቅና ስንቅ ብሎም በሀሳብ የማደራጀትና ለድል የማብቃት ጉልህ ሚናችሁ እስከ ዘላቂ ነጻነት ድረስ ተጠናክሮ እንዲቀጥል በአማራ ህዝብና በሀገራችን ኢትዮጵያ ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።


በመጨረሻምወንድማችን አርበኛ ፋኖ ዘመነ ካሴን እንኳን ከጠባቡ እስር ቤት ወደ ሰፊው እስርቤት እግዚአብሄር በደህና አመጣህ እያልን በቀጣይም የተጀመረው የአማራ ህዝብ የህልውና ትግል ለድል ይበቃ ዘንድ ያለህን የመሪነት ሚና አጠናክረህ እንድትቀጥል እንፈልጋለን።

አማራበልጆቹ ትግል ህልውናውን አረጋግጦ የተቀማውን ሀገሩን ኢትዮጵያን ያስመልሳል። የሀገሩ ባለቤትም ይሆናል።

ምስራቅ አማራ ፋኖ

ግንቦት 29 ቀን 2015 ዓ.ም


Recent Posts

See All

ከአማራ ፋኖ አንድነት በወሎ ላስታ አውራጃ አሳመነው ብርጌድ የተሰጠ አስቸኳይ መግለጫ

በዐብይአህመድ አሊ የሚመራው የብልጽግና መንግስት በአማራ ክልል በአውሮፕላን ቀረሽ ጦርነት እየፈጸመ ባለው ወረራ፣ ግድያ እና ማፈናቀል በንፁሁ የአማራ ህዝብ እና የሀይማኖት ተቋማቱ ላይ መጠነ ሰፊ ጥፋት ፈጽሟል።...

コメント


bottom of page