top of page

የአማራ ሕዝብ ትግል ከፍ ወዳለ ደረጃ መሸጋገርን አስመልከቶ የተሰጠ አስቸኳይ መግለጫ

የአማራ ሕዝብ በደምና አጥንቱ ባፀናት አገሩ ላለፉት 50 ዓመታት ሥርዓት ወለድ በሆነ ችግር በማንነቱ ሲጨፈጨፍ፣ ሲፈናቀል፣ ሲሰደድና በሴራ ከአገሪቱ ፖለቲካ እንዲገለል በማድረግ ከምጣኔ ሀብታዊና ማህበራዊ ጥቅሞች ውጭ ሆኖ ቆይቷል።ይባስ ብሎ ላለፉት ዓመታት በለውጥ ስም የኢትዮጵያን መንበረ ዙፋን የተቆጣጠረውና በጥላቻ ያደገው የዘረኛው ህዎሓት የበኩር ልጅ ኦህዴድ/ኦነግ በስልጠና፣ በትጥቅና በስንቅ ባደራጃቸው ገዳይ ኃይሎቹ አማራውን ያለርህራሄ በጥይትና በገጀራ በመጨፍጨፍ የዘር ማጥፋት ፈፅመዋል። ሀብት ንብረቱን ዘርፈውና አውድመው ከሚኖርበት አካባቢ በማፈናቀል የዘር ማፅዳት ፈፅመዋል፤ ቅድመ አያቶቹ ባቀኗት ከተማ አዲስ አበባ እንዳይገባ ከልክለዋል፣ በኢትዮጵያ ሰማይ ሥር ተዘዋውሮ እንዳይሠራ መንገድ ላይ እያገቱ ዘርፈዋል፣ ገድለዋል።


አሁን አሁን ደግሞ ከመዝረፉና መግደሉ ባሻገር ህፃናትን ሁሉ ሳይቀር እያገቱ "ማስለቀቂያ" በሚል ዘዴ ከድሃ የአማራ እናቶች መቀነት በሚሊዬን ገንዘብ ይቀበላሉ፤ የአማራ ባለሃብቶች የባንክ አካውንቶችን አግደዋል። አርሶ አደሩ በጉልበቱ ዘርቶ እንዳይጠቅም በተጠና መንገድ የአፈር ማዳበሪያ በመከልከል ማሳው ጦም እንዲያድር አድርገዋል።


ይህ ሀሉ አልበቃ ያለው ፈሽስቱ የኦህዴድ/ኦነግ ሥርዓት ላለፋት አራት ወራት "ህግ ማስከበር" በሚል ሽፋን በአማራ ክፍለሀገር በመከላከያ ስም የተደራጀ የአንድ ዘር ታጣቂ ሰራዊት በማዝመት የዕምነት ተቋማትን አውድሟል፣ ሴቶችን ደፍሯል፣ንፁሃንን ገድሏል፣ አሁንም ስፍር ቁጥር የሌለው ሰራዊት ወደ አካባቢው እያስገባ ይገኛል።


ይህ ሁሉ በደል የተፈጸመበት የአማራ ሕዝብ የጀመረውን የህልውና ትግል ከፍ ወዳለ ደረጃ በማድረስ ከሐምሌ 24/2015 ዓ.ም ጀምሮ ከተሞችን ከፋሽስቱ ኦህዴድ/ኦነግ ብልፅግና መዋቅር በክንዱ ነፃ እያወጣ ከተሞችን እየተቆጣጠረ ይገኛል።


በተለይም በጎጃም፣ በጎንደር፣ በወሎና በሸዋ አብዛኛውን ከተሞች ፋኖ ከሕዝቡ ጋር በመቀናጀት የአሽከሩን ብአዴን ብልፅግና መዋቅር በመበጣጠስ በአስገራሚ ፍጥነት እና ብቃት እየተቆጣጠራቸው ይገኛል።


በመሆኑም የአማራ ሕዝባዊ ግንባር የሚከተለውን ጥሪ ያስተላልፋል:-


1ኛ) የአማራ ሕዝብ በጀግኖች ልጆቹ የጀመረውን የገዥውን ሥርዓት መዋቅር እየበጣጠሰ ከተሞችን የመቆጣጠር ጎዞውን አጠናክሮ እንዲቀጥል፤


2ኛ) የአማራ ሕዝብ የጀመረውን በክንዱ ነፃ የመውጣት ጉዞ ለማደናቀፍ በኩሊው ብአዴን በኩል ሐምሌ 27/2015 ዓ.ም ከምሽቱ 1 ሰዓት ጀምሮ ክልሉ ከቁጥጥራቸው ሥር እንደወጣ በይፋ በመግለፅ ተጨማሪ የሥርዓቱ ገዳይ ኃይል እንዲገባና ንፁሃንን እንዲጨፈጭፍ ፈቅደዋል። ክልሉም በወታደራዊ አገዛዝ ሥር እንዲወድቅ አዝዘዋል። ስለሆነም በአማራ ክልልም ይሁን ከክልሉ ውጭ የሚገኝ ማንኛውም ታጣቂ ፋኖ፣ የአማራ ልዮ ኃይል፣ የአማራ ፖሊስ፣ አድማ ብተና፣ ምልስ የሰራዊቱ አባላት፣ የሚሊሻ አባላትና ሌሎችም በሙሉ ከዛሬ ጀምሮ በክልሉ ያለው የሥርዓቱ መዋቅር መፍረሱን በመረዳት ከአማራ ሕዝብ የህልውና ትግል ጎን እንድትሰለፉና ታሪካዊ ኃላፊነታችሁን ትዎጡ ዘንድ ግንባሩ ጥብቅ ጥሪ ያደርጋል።


3ኛ) የመከላከያ ሰራዊት አባላት በሙሉ የኦህዴድ/ኦነግ ፋሽስቱ ሥርዓት ለግል ጥቅሙና ስልጣኑ ሲል ትናንት በእርስ በርስ ጦርነት በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ጓዶቻችሁን አስጨፍጭፏል፤ የተጨፈጨፉ ጓዶቻቸሁ አስክሬን በወግ ተሰብስቦ ለአፈር ሳይበቃ ከገዳዮቻችሁ ጋር "በሰላም ስምምነት ስም" ክህደት ፍፅሞባችኋል። ዛሬ ደግሞ ይባስ ብሎ በክፉ ቀን ያበላ፣ ያጠጣችሁንና የሸሸጋችሁን ሕዝብ እንድትዎጉ ተገዳችኋል። ትዕዛዙን ባለመቀበል እየከዳችሁ ከአማራ ኃይሎች ጎን እንድትሰለፉ ጥሪ እናቀርባለን።


4ኛ) በአገዛዙ ስቃይና መከራ ውስጥ የምትገኘው ሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብ ከአማራ ህዝብ የህልውና ትግል ጎን እንድትቆም ጥሪ ቀርቧል።


5ኛ) በስተመጨረሻም የአማራና የኢትዮጵያ ሕዝብ ዘብ የሆንከው ጀግናው የአማራ ፋኖ ከሕዝብህ ጋር የጀመርከውን የነፃነት ጉዞ አጠናክረህ እንድትቀጥል ጥሪ እያቀረብን የአማራ ሕዝባዊ ግንባር በቀጣይ ሁለት ቀናት ውስጥ ላልተወሰነ ጊዜ የሚቆይ ኮማንድ ፖስት የሚያቋቁም መሆኑን ይገልፃል።


ኮማንድ ፖስቱ በመላው የአማራ ከተሞች የሚተገበር ሆኖ የአማራን የህልውና የነፃነት ትግሉን ማቀጣጠልና ነፃ የወጡትን የአማራ የቀበሌ፣ የወረዳ፣ የዞን አውራጃዎችንና ከተሞችን በሚቋቋመው ኮማንድ ፖስት በተመደቡ የአማራ የትግል አካላት እንዲተዳደሩና ህዝቡም አካባቢውን እንዲጠብቅ ደንብ ተዘጋጅቷል።በተጨማሪም ስለንብረትና እስረኛ አጠባበቅን በተመለከተ በኮማንድ ፖስቱ ተካቶ ደንቡ ይፋ ይሆናል።


ድል ለአማራ ሕዝብ!


መነሻችን የአማራ ሕልውና፣


መዳረሻችን የኢትዮጵያ አንድነት


የአማራ ሕዝባዊ ግንባር!




17 views0 comments

Comments


bottom of page