top of page

የአማራን ሕዝብ የህልውና ትግል የሚያቀናጅ ኮማንድ ፖስት ተቋቋመ!

Updated: Aug 29, 2023

የአማራ ሕዝብ ላለፉት ረጅም ዓመታት እንደ ሕዝብ ሲደርስበት የነበረውን መስፈሪያ-የለሽ መከራ፣ አገርና ሕዝብን ለማቆየት ሲል ስቃዩን ችሎ ሰላማዊ የለውጥ ሁኔታ ይፈጠራል በሚል ሲታገስ ቆይቷል። ትዕግሥቱን ፍርሃት፣ ዝምታውን የተሸናፊነት፣ መንግሥት ማክበሩን እንደ አላዋቂነት ተወስዶ በመከራ ላይ መከራ ሲደራረብበት ቆይቷል። ይህ ሁሉ የአማራው ታጋሽነት የአገርን ሕልውና ከአደጋ ለመጠበቅ፣ የንጹሃን እልቂትን ለማስቀረትና በሰላማዊና ሕጋዊ መንገድ መፍትሄ ይገኛል ከሚል ፍጹም ስልጡንነት ነበር። ሆኖም የአብይ አህመድ የኦሮሙማ የፓለቲካ አይድዮሎጂን ተከትሎ፣ የአማራውን ሕህዝብ፣ ከክርስትናና ከሙስሊም እምነት ተከታዮች ጋራ አጥፍቶ፣ በምስራቅ አፍሪካ የኩሽ ግዛት ለመፍጠር የጀመረው የፋሺዝም የዘር ማፅዳትና የመስፋፋት ፓሊሲ ከኢትዮጵያም አልፎ በመላው አፍሪካ ቀንድ አገሮች ላይ ታላቅ የፀጥታ ችግር ፈጥሮ፣ ቀጠናውን የኃያላን ጦር አውድማ ሳያደርገው ኢንተርናሽናል ኮሚኒቲው አስፈላጊውን ትኩረት ሊሰጠው ይገባል።


ይህ የጉግማንጉግ ሰው-በላ የአራዊት አገዛዝ ለሠላም የተዘረጋውን የሕዝባችንን እጅ ለመቁረጥ ምሳሩን መዞ እልቂትን አውጇል። ዐማራው ህልውናውን ለመከላከል ያለው ብቸኛ አማራጭ ኃይል ብቻ በመሆኑ ሳይወድ በግድ በጠላቶቹ ጋባዥነት ወደ ለየለት ጦርነት ውስጥ ገብቷል። የአማራ ሕዝብ በአሁኑ ወቅት የአብይ አህመድ የኦሮሙማ-ኦህዴድ-ኦነግ አገዛዝን ወረራ ለመመከት በበርካታ ግንባሮች እየተፋለመ ይገኛል። ሕዝባችን እየተፈጸመበት ያለውን መረን-የለሽ ጭፍጨፉ፣ አፈናና ግድያ ዝም ብሎ ከመመልከት ወደ ሁለገብ የተከላካይነት ምዕራፍ ተሸጋግሯል። የተጋድሎው ግለትና የጦር ግንባሩ ስፋት አማራው የሚያደርገውን ትግል በበለጠ ውጤታማና አሸናፊ እንዲሆን የተቀናጀ አመራር የሚሰጥ አካል ማዋቀር አስፈልጏል።


ይህንንም የሚያቀናጅ ኮማንድ ፖስት ተቋቁሟል።


የአማራው የተለያዩ ክፍላተ አገሮች፣ በሥራቸው የፋኖ ብርጌዶች ያሏቸው ኮማንድ ፖስቶች ሲኖሯቸው፣ እነዚህንም በበላይነት የሚያስተባብረው ጀግናው አርበኛ ሉቴናንት ኮረኔል ፉንታሁን ሙሃባ ነው።


የኮማንድ ፖስቱ ዓላማዎች፡


1. ክልሉን ሙሉ በሙሉ ከጠላት ለማፅዳት የተባበረና የተቀነባበረ ትግል እንዲካሄድ ማድረግ፤


2. ትግሉን ለመቀላቀል የሚፈልጉ ኃይሎችን ማሰልጠን፣ ማስታጠቅና ለትግል ማሰማራት፤


3. የሎጅስቲክስ አቅርቦትን ለማሳለጥና፣ ጉዳት የደረሰባቸውን በመንከባከብ እርዳታ እንዲያገኙ ማመቻቸት፤


4. የጠላት ምርኮኞችንም ዓለም ዓቀፍ ህግ በሚፈቅደው መሠረት መጠብቅ፣


መነሻችን የአማራ ሕልውና፣


መዳረሻችን የኢትዮጵያ አንድነት


ከአማራ ሕዝባዊ ግንባር የተሠጠ አስቸኳይ መግለጫ


25 views0 comments

Comments


bottom of page