top of page

የኦሮሙማ ብልፅግናን ዓላማ ለማሳካት በጥናት የተመረጡ ግለሰቦች ስብስብ በሆነው ፓርላማ ስብሰባ ላይ በአንዳንድ አባላት የተሰጠው ማብራሪያ የአማራን የህልውና

Updated: Aug 29, 2023

የአማራን ሕዝብ ለማጥፉት በእብሪት ሠራዊቱን ያዘመተው የዘረኛውና ሰውበላው የኦሮሙማ ብልፅግና ፋሽስታዊ አገዛዝ በግፍ የጀመረውን ጦርነትና በአማራ ሕዝብ ላይ የጣለውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሕጋዊ ሽፉን ለመስጠት የጠራው የፓርላማ ስብሰባ ላይ የራሱ ጎምቱ አባላት ሕገወጥና ፀረ-ሕዝብ ለመሆኑ በአደባባይ ሲመሰክሩ አይተናል።


በአማራ ሕዝብ ላይ የተጣለውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በተመለከተ በፓርላማው ውሏችሁ የስብሰባ አካሄዳችሁን ከሕዝብ ጥያቄ አንፃር ለማመሳሰል የሞከራችሁ አባላት አቋማችሁን በአወንታዊ ብንመለከተውም ፀረ-ሕዝብ፣ ፀረ-እምነት፣ ፀረ-ኢትዮጵያ የሆነውን ፋሽስታዊ አገዛዝ ሕጋዊና ተቀባይነት እንዲያገኝ ለማድረግ ካበረከታችሁት አስተዋፅዖ ጋር ሲነፃፀር ልክ በባህር ላይ ጠብ እንዳለች የውሃ ጠብታ ግምት ውስጥ የሚገባ አይደለም።ማድረግ የነበረባችሁ ቢያንስ ቢያንስ የዛሬ አራት ዓመት ፓርላማውን ጥላችሁ መውጣት ነበረባችሁ።ምንም እንኳን እጅግ የረፈደ ቢሆንም ዛሬም ለናንተ ያለን ምክር ጧትና ማታ በማንነቱ ለሚጨፈጨፈው ወገናችሁ ስትሉ ፓርላማ ተብዬውን ከማድመቅ ይልቅ ባስቸኳይ ጥላችሁ እንድትወጡ ነው።


በተለያየ መንገድ የአብይ አህመድን ፀረ-አማራ አገዛዝ እያገለገላችሁ ያላችሁ የአማራ ተወካዮች ሆይ! የሕወሃትና የኦሮሙማ ግፍ የወለደው የአማራ ሕዝብ ተጋድሎ ከፍተኛ መስዋእትነት እየተከፈለበት ወደፊት እየገሠገሠ ነው።


እናንተም ጊዜው ሳይረፍድባችሁ አቋማችሁን በማስተካከል በአካልም በመንፈስም ከወገናችሁ ጎን ተሰለፉ።


ውድ አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በሙሉ! የአማራው ወገናችሁ ትግል ዛሬ ላይ የህልውና ትግል ቢሆንም ውሎ አድሮ የጋራ አገራችንን ኢትዮጵያን እንደ ሃገር የሚያስቀጥል ትግል ስለሆነ በያላችሁበት የድርሻችሁን እንድትወጡ ጥሪያችንን እናቀርብላችኋለን። ኦሮሙማ የናንተንም ቤት እያንኳኳ እንደሆነ አ በተግባር እየታየ ነው።


የዛሬ ዝምታችሁ ነገ የሚጠቅመው እናንተን ሳይሆን ሰው በላውን ሥርዓት እንደሆነ መነገር ያለባችሁ አይመስለንም። ስለዚህ በያላችሁበት ዘረኛውን የአብይ አህመድን ሥርዓት እንድትፋለሙት ጥሪያችንን እናቀርብላችኋለን። ድል ለሕዝባችን!


የአማራ ሕዝብ ያሸንፋል፦


መነሻችን የአማራ ህልውና

መዳረሻችን የኢትዮጵያ አንድነት፦


የአማራ ሕዝባዊ ግንባር





45 views0 comments

Comments


bottom of page