top of page

የጀግናው ሻለቃ ውባንተ መሰዋት ትግሉን እንደሰደድ እሳት በማቀጣጠል የኦሮሙማን ውድቀት እያፋጠነው ነው!

ከአማራ ፋኖ ህዝባዊ ሰራዊት የውጭ ድጋፍ ሰጭ ግ/ሃይል የተሰጠ መግለጫ

( 3/26/2024)


ጀግናው ሻለቃ ውባንተ አባተ የጉና ክ/ጦር ዋና አዛዥ የአማራን ህልውና ለማረጋገጥ ከወራሪው የአብይ አህመድ የኦነግ ሠራዊት ጋር ሲፋለም ከተሰዋ ሳምንት ሆኖታል። በጊዜው የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ሠራዊት አመራር ፋኖ አርበኛ እስክንድር ነጋ ስለሻለቃ ውባንተ አባተ መሰዋት የተሰማንን ጥልቅ ሃዘን በድርጅታችን ስም ከሚገኝበት ከትግል ሜዳ ወዲያው በቪድዮ አጠር ያለ መልእክት ማስተላለፉ ይታወሳል።


ሻለቃ ውባንተ አባተ ይህ ዛሬ ስልጣን ላይ ያለው ፋሺስታዊው የብልጽግና ወንበዴ ቡድን ወደ ስልጣን ከመጣበት ከ2018ቱ ህዝባዊ ትግልና ለውጥ በፊት በህወሃት መራሹ የኢህአዴግ ሥርዓት ላይ “እንቢ ለመብቴ፤ እንቢ ለነጻነቴ!’ ብሎ በመነሳት ከነበረበት የፌዴራል ፖሊስ ሃላፊነት ለቆ ለትግል ጫካ በመግባት ትግሉን የጀመረ ጀግና ታጋይ ነበር፡፡ ስለሆነም ሻለቃ ውባንተ አባተ የህወሃት መራሹን የኢህአዴግን ሥርዓት አንኮታኩቶ በገረሰሰው ፊልሚያ ውስጥ ከትግል አጋሮቹ ጋር ወሳኝ ሚና በመጫወት አሻራውን ያሳረፈ የቁርጥ ቀን የህዝብ ልጅ ነበር፡፡


የአማራ ህዝብ እያደረገ ባለው የህልውና ትግል ላይ ጀግናው ሻለቃ ውባንተ የጉናን ክፍለ ጦር በመምራት ለወገን እጅግ የሚያኮራ ለጠላት እጅግ የሚያስጨንቅና የሚያስፈራ ወሳኝ ትግል በማድረግ የሚታወቅ ጀግና ነበር፡፡


ጀግናው ሻለቃ ውባንተ አባተ ለገባው ቃል ኪዳን ታምኖ እስከመጨረሻው ድረስ በመጓዝ ምትክ የለሽ ውድና ብርቅዬ ህይወቱን ሰውቶልናል፡፡ የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ሰራዊት የሻለቃ ውባንተን መሰዋት ምክንያት በማድረግ የተሰዋለትን የአማራን ህልውና የማረጋገጥ ዓላማ ከሌሎች ፋኖ አደረጃጀቶች ጋር በመሆን ከግብ ለማድረስ ስንቋቋም የገባነውን ቃል ኪዳን እንደገና እናረጋግጣል። አዎ ጀግኖቻችን የአማራ ፋኖዎች የተሰውለትን ዓላማ ከግብ የማድረስ አማራዊ፣ ሃገራዊ፣ ሃይማኖታዊና ታሪካዊ ግዴታ እንዳለብን ምንጊዜም ቢሆን የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ሰራዊት በጽኑ ያምናል፡፡


የጀግናውን መስዋእትነት ዜና መሰማትን ተከትሎ በመላው የፋኖ አደረጃጀቶች ውስጥ የተቀሰቀሰው ምድር አርድ ቁጣና ንዴት ትግላችን ግቡን ሳይመታ እንደማይበርድ እሙን ነው። ስለሆነም በአራቱም የአማራ ግዛቶች በጀግናው ስም የተሰየመው “ዘመቻ ውባንተ” በመጧጧፍ ላይ ይገኛል፡፡ ባለፉት ቀናቶች የፋሽስቱ አብይ አህመድ ከፍተኛ የጦር መሪዎች በፋኖ እስከወዲያኛው እየተሸኙና ወይም እየቆሰሉ እንዲሁም በተለያዩ የጦር አውዶች እየተማረኩ ነው። የአማራን የህልውና ትግል ለመቀልበስ በተሰማሩ ሆድ አደር ባንዳ ሚሊሽያዎችና አድማ ብተና ፖሊሶችም ላይ ፋኖ የማያዳግም እርምጃ እየወሰደባቸው ይገኛል።


ወንድማችን፣ ታግሎ አታጋዩ ጓዳችን ሻለቃ ውባንተ አባተ ለቆመለት የተቀደሰ ዓላማ በመሰዋቱ መንፈሳዊ ቅናት፣ ቁጭት፤ እልህና ንዴት በውስጣችን ፈጠረብን እንጂ በሃዘን አንገታችን አልተሰበረም። ይልቅ የሻለቃ ውባንተን ተምሳሌነት አንግበን በገባነው ቃልኪዳንና በተለምነው ግብ መሠረት አስፈላጊውን መስዋእትነት በመክፈል አራት ኪሎ መግባታችን አይቀሬ ነው። በደሙ ስሙን የፃፈው ጀግናው ወንድማችንም በተከታታይ ትውልዶች ሲዘከር ይኖራል።


ታጋይ ይሰዋል፤ትግል ግን እስከ ድል ይቀጥላል!!

ዘላለማዊ ክብር ለሰማእታቶቻችን!!


መነሻችን የአማራ ህልውና

መዳረሻችን የኢትዮጵያ አንድነት!!

31 views0 comments

留言


bottom of page