top of page

ዶ/ር ልዑል አስፋወሰን አሥራተ ካሳ የግንባሩን የውጭ ጉዳይ በአውሮፓና አፍሪካ ለማስተባበር ሃላፊነት ወሰዱ

በሻለቃ ዳዊት ወ/ጊዮርጊስ የአማራ ሕዝባዊ ግንባር የውጪ ድጋፍ አስተባባሪና በዶ/ር ልዑል አስፋወሰን አሥራተ ካሳ ጋር በተደረገው ምክክር መልካም ፍቃዳቸው ሆኖ በሻለቃ ዳዊት የቀረበላቸውን ሐሳብ ተቀብለው “የአማራ ሕዝባዊ ግንባርን” ወክለው በመላው አውሮፓ እንዲሁም በአፍሪካ የግንባሩ የውጭ ጉዳይን ሙሉ ሃላፊነትን ወስደው ለማቀነባበር መስማማታቸውን ስናበስር በታላቅ ደስታ ነው። በዚህም ውሳኔአቸው በዓለም አቀፍ የሚደረገውን ትግል ወደተለየ ከፍታ አሸጋግረውታል።


ዶ/ር ልዑል አስፋወሰን አሥራተካሳ አዲስ አበባ በ1948 ተወለዱ። እዚያ በሚገኘው የጀርመን ትምህርት ቤት የጀርመን የከፍተኛ ትምህርት መግቢያን በማለፍ በአውሮፓ በጀርመን ቱቢንገን እና በእንግሊዝ ካምብሪጅ ዪኒቨርስቲዎች ታሪክ እና ህግን የተማሩ ሲሆን የዶክትሬት ዲግሪያቸውን በፍራንክፈርት በጎተ ዩኒቨርስቲ ሠርተዋል። በጀርመን አገር ቆይታቸው ላይ በጋዜጠኝነት እና በፕሬስ ኦፊሰርነት ያገለገሉ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ለአፍሪካ እና ለመካከለኛው ምስራቅ የንግድ አማካሪ በመሆን ይሠራሉ። በጀርመንኛ ቋንቋ አንቱታን ያተረፉላቸው ከአሥር (10) በላይ መጽሐፍትን ያሳተሙ ሲሆን በተለይ ደግሞ “Manieren” (ስነሥርዓት) የተሰኘው መፅሐፋቸው በሃያሲዎች ዘንድ ከፍተኛ ዝናን አትርፎላቸዋል። የተለያዩ ሽልማቶችንም አስገኝቶላቸዋል።


ለብዙ ዓመታት በአፍሪካ በተለይም በሀገራቸው ኢትዮጵያ ውስጥ አዲስ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ሥርዓት እንዲኖር ቁርጠኛ በመሆን በአውሮፓ ጆርናሎች ላይ በርካታ ጽሑፎችን አሳትመዋል። በጀርመን አገር የተለያዩ እውቅና እና ሽልማቶችን አግኝተዋል። በ2004 አደልበርት ቮን ቻሚሶ ሽልማት ለ”ስነሥርዓት” ምጽሓፋቸው ተሸልመዋል። በ2010 የቱቢንገን ዩኒቨርሲቲ የክብር ሴናተር ሆነዋል። በ2011 የዋልተር ሼል የፌዴራል ኢኮኖሚ ትብብር እና ልማት ሚኒስቴር ሽልማት አግኝተዋል። በ2015፡ የያዕቆብ ግሪም ሽልማት፤ በ2016፡ የክብር መስቀል ከሪባን ጋር፤ በ2019፡ 1348th Knight of the Order of the Austrian Golden Fleece ማእረግ ሲሰጣቸው፤ የፌዴራል ኢኮኖሚ ትብብር እና ልማት ሚኒስቴር የኢኖቬሽን አማካሪ ቦርድ አባል፤ የዮሃን ዎልፍጋንግ ጎተ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ተማሪዎች ምክር ቤት አባል፤ የORBIS AETHIOPICUS የኢትዮጵያ ባህል ጥበቃና ማስፋፊያ የባለአደራ ቦርድ መሥራች እና ሰብሳቢ፣ የኢትዮጵያ ሙዚዬሞች ማህበር የቦርድ ሰብሳቢ፤ የሲቭል ነፃነት በኢትዮጵያ የመማክርት ፕሬዚደንት በመሆን እያገለገሉ ይገኛሉ።


መነሻችን የአማራ ሕልውና፣


መዳረሻችን የኢትዮጵያ አንድነት !!!


የአማራ ሕዝባዊ ግንባር!!


12 views0 comments

コメント


bottom of page